ማስታወቂያ

programs top mid size ad

መስከረም 19፣2013/ የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ ለህዝብ እና ቤቶች ቆጠራ ተብሎ ከ9 መቶ ሚሊየን ብር በላይ ወጪ ተደርገው የተገዙለትን ታብሌቶች ለተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ማከፋፈሉን ተናገረ

የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ ለህዝብ እና ቤቶች ቆጠራ ተብሎ ከ9 መቶ ሚሊየን ብር በላይ ወጪ ተደርገው የተገዙለትን ታብሌቶች ለተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ማከፋፈሉን ተናገረ፡፡

በ2012 ይካሄዳል ተብሎ ለነበረው የህዝብ እና ቤቶች ቆጠራ አገልግሎት ተገዝተው የነበሩት ታብሌቶች 180,000 መሆናቸውን የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ዋና ዳይሬክተር አቶ ቢራቱ ይገዙ ለሸገር ነግረዋል፡፡
  
ታብሌቶቹ በተለያዩ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ጥቅም ላይ እንዲውሉ እየተከፋፈሉ ያሉት ሀገር አቀፍ የህዝብ እና የቤቶች ቆጠራው በመራዘሙ ምክንያት ነው ብለዋል፡፡

ከ900 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የወጣባቸው መሳሪያዎች ከጊዜ ብዛት እንዳይበላሹ ለተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ተከፋፍለዋል ተብሏል፡፡ የታብሌቶቹ ግዢ በወቅቱ ከሀገረ ቻይና እንደተፈፀመ የጠቀሱት ዋና ዳይሬክተሩ፤ አቅራቢዎቹም ሁዋዌይ እና ሌኔቮ የተባሉ የቻይና ኩባንያዎች እንደሆኑ ነግረውናል፡፡

ከተገዙ 3 ዓመት የሞላቸውን ታብሌቶች ከተሰጧቸው መንግሥታዊ መስሪያ ቤቶች ውስጥ አንዱ ግብርና ሚኒስቴር እንደሆነ ሰምተናል፡፡ ሸገር ይህንኑ ለማረጋገጥ ግብርና ሚኒስቴር ደውሎ ጠይቋል፡፡ የግብርና ሚኒስቴርም ከማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ 35,410 ታብሌቶችን መረከቡን ነግሮናል፡፡

 

ቁልፍ ቃላት
ምላሽ