ማስታወቂያ

programs top mid size ad

መስከረም 20፣2013/ የአደባባይ ምሁሩ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ትናንት ለሊት ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

የአደባባይ ምሁሩ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ትናንት ለሊት ከዚህ አለም በሞት ተለዩ።

የአደባባይ ምሁሩ፣የጂኦግራፊ መምህር፣ፖለቲከኛ፣ደራሲ፣የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ከዚህ አለም በሞት መለየታቸውን ሸገር ሰምቷል።

ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ዕድሜያቸውን ሙሉ ለኢትዮጵያ ይበጃል ያሉትን ሁሉ ፊት ለፊት ከመናገር የማየቦዝኑ በመሆናቸው ይታወቀሉ። 

ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በመምህርነት፤በተመራማሪነት አገልግለዋል፡፡

በውጪ አገር ዩኒቨርስቲዎችም አስተምረዋል፡፡ በጊምቢ አውራጃ አስተዳዳሪነትም ሰርተዋል፡፡በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የተመሰረተውን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ጉባኤ መስርተውና መርተው የህዝባቸውን የሰብአዊ መብት እንዲከበር በብዙ ደክመዋል፡፡

ፕሮፌሰር መስፍን እስከ ህይወታቸው ፍጻሜ በመገናኛ ብዙሃን ስለሃገራቸው እድገትና ስለህዝባቸው ደህንነት አስተያየት ከመጻፍ ያላቋረጡ ምሁር ነበሩ፡፡

ሸገር በፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ህልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን እየገለፀ ለወዳጅ፣ዘመዶቻቸው እና ለአፍቃሬ ኢትዮጵያውያን በሙሉ መጽናናትን ይመኛል!

ቁልፍ ቃላት
ምላሽ