ማስታወቂያ

programs top mid size ad

ህዳር 16፣2013/ አርጀንቲናዊው የእግር ኳስ ኮኮብ ዲያጎ አርማንዶ ማራዶና ከዚህ አለም በሞት ተለየ

አርጀንቲናዊው የእግር ኳስ ኮኮብ ዲያጎ አርማንዶ ማራዶና ከዚህ አለም በሞት ተለየ። 

ማራዶና ህይወቱ ያለፈችው በ60 ዓመቱ መሆኑን BBC አውርቷል። የቀድሞው ኮኮብና አሰልጣኝ በቅርቡ የጭንቀት ደም መርጋት ቀዶ ህክምና ማድረጉን የወሬ ምንጩ ፅፏል።

ከአለማችን የእግር ኳስ ኮከቦች መካከል ስሙ ጎልቶ የሚነሳው ማራዶና ሀገሩ አርጀንቲና የ1986ቱን የአለም ዋንጫ ስታነሳ ቡድኑን በአንበልነት መርቷል። አርማንዶ ማራዶና ለስፔኑ ባርሴሎና እንዲሁም ለጣሊያኑ ናፖሊ ተጫውቶ አሳልፏል።

ሀገሩን በ4 የአለም ዋንጫ ወክሎ የተጫወተው ኮኮቡ ለሀገሩ በተጫወተባቸው 91 ጨዋታዎች 34 ጎሎች አስቆጥሯል። ማራዶና ከተጫዋችነቱ በተጨማሪ ሀገሩን በአሰልጣኝነት አገልግሏል ፣የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ እና ሜክሲኮ አገር ክለቦችንም አሰልጥኗል።

ቁልፍ ቃላት
ምላሽ