ማስታወቂያ

programs top mid size ad

ጥር 4፣ 2013/ ተመራጩ ፕሬዝዳንት ጆ ይይደን የአሜሪካውን ማዕከላዊ የስለላ ድርጅት (CIA) የበላይ መረጡ

Image
Joe-Biden

ተመራጩ ፕሬዝዳንት ጆ ይይደን የአሜሪካውን ማዕከላዊ የስለላ ድርጅት (CIA) የበላይ መረጡ፡፡ በጆ ባይደን የCIA ዋና ዳይሬክተር ሆነው የተመረጡት ዊሊያም በርንስ እንደሆኑ ቢቢሲ ፅፏል፡፡

ዊሊያም በርንስ በቀደሞው ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ የአስተዳደር ዘመን ከኢራን ጋር የተደረገውን ኒኩሊየር ነክ ድርድር በመሪነት ማከናወናቸውን መረጃው አስታውሷል፡፡

ከዚያ በኋላ በሰላም እና በአካባቢ ጥበቃ ላይ ያተኮረ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ሲመሩ ቆይተዋል፡፡ በመንግሥታዊ ተግባራት አከናዋኝነትም የ33 ዓመታት ልምድ ያካበቱ እንደሆኑ ተነግሮላቸዋል፡፡

ጆ ባይደን በመጪው ጥር 12 ቀን በሚከናወነው በዓለ ሲመታቸው ቃለ መሐላ በመፈፀም 46ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት እንደሚሆኑ ይጠበቃል፡፡ ቀስ በቀስም የአስተዳደራቸውን የወደፊት ሹሞች እወቁን ማለታቸውን ቀጥለዋል፡፡

ቁልፍ ቃላት
ምላሽ