ማስታወቂያ

programs top mid size ad

ጥር 4፣ 2013/ የአለም የጤና ድርጅት መርማሪዎች ለሚጠብቃቸው የምርመራ ተልዕኮ ከነገ በስቲያ ቻይና ይደርሳሉ ተባለ

Image
WHO

የአለም የጤና ድርጅት መርማሪዎች ለሚጠብቃቸው የምርመራ ተልዕኮ ከነገ በስቲያ ቻይና ይደርሳሉ ተባለ፡፡

የድርጅቱ የጤና መርማሪዎች የኮሮና ቫይረስ መነሻ ጉዳይ የማጣራት ተልዕኮ አላቸው መባሉን አሶሼትድ ፕሬስ ፅፏል፡፡ መርማሪዎቹ ዋነኛዋ ትኩረታቸው በማዕከላዊ ቻይና የምትገኘው የውሃን ከተማ እንደሆነች ታውቋል፡፡

ውሃን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መነሻ ተደርጋ እንደምትቆጠር መረጃው አስታውሷል፡፡ በቻይና የአለም የጤና ድርጅት ተቆጣጣሪዎችን ተልዕኮ ለማስፈቀድ ረዘም ላለ ጊዜ ድርድር ሲካሄድ ቆይቷል ተብሏል፡፡

ባለፈው ሳምንት ታስቦ የነበረው የጤና መርማሪዎቹ ጉዞ መስተጓጎሉ የአለም የጤና ድርጅትን አስቆጥቶት እንደነበር በመረጃው ለትውስታ ተጠቅሷል፡፡

ቁልፍ ቃላት
ምላሽ