ማስታወቂያ

programs top mid size ad

የካቲት 15፣ 2013/ ንብረትነቱ የናይጄሪያ አየር ሀይል የሆነ አነስተኛ የመጓጓዣ አውሮፕላን በመከስከሱ በውስጡ የነበሩ 7 ሰዎች መሞታቸው ተሰማ

ንብረትነቱ የናይጄሪያ አየር ሀይል የሆነ አነስተኛ የመጓጓዣ አውሮፕላን በመከስከሱ በውስጡ የነበሩ 7 ሰዎች መሞታቸው ተሰማ፡፡

አውሮፕላኑ ከርዕሰ ከተማዋ አቡጃ በስተሰሜን በ110 ኪሎ ሜትር ርቀት ወደምትገኘዋ ሚና በማምራት ላይ በነበረበት ወቅት የሞተር እክል እንደገጠመው መነገሩን ሬውተርስ ፅፏል፡፡

አደጋው የገጠመው ወደ አቡጃ ኤርፖርት ተመልሶ ለማረፍ ሙከራ ባደረገበት ወቅት ነው ተብሏል፡፡ የአገሪቱ የአየር ሀይል አዛዥ የአደጋው ምክንያት በዝርዝር እንዲመረመር ማዘዛቸው ተሰምቷል፡፡

በአደጋው የሞቱት ሰዎች ማንነት አልተጠቀሰም ተብሏል፡፡ የመከስከስ አደጋ የገጠመው አውሮፕላን የቴክስትሮን አቪየሽን ኩባንያ ስሪት መሆኑ ታውቋል፡፡


 

ቁልፍ ቃላት
ምላሽ