ማስታወቂያ

programs top mid size ad

መጋቢት 28፣ 2013- አሜሪካ በኢራን የኒኩሊየር መርሐ ግብር ጉዳይ በቬየና ኦስትሪያ በሚካሄደው ቀጥተኛ ያልሆነ ንግግር መካፈል መጀመሯ ተሰማ

አሜሪካ በኢራን የኒኩሊየር መርሐ ግብር ጉዳይ በቬየና ኦስትሪያ በሚካሄደው ቀጥተኛ ያልሆነ ንግግር መካፈል መጀመሯ ተሰማ፡፡

ንግግሩ ከዚህ ቀደም የተደረሰውን ስምምነት ከፍፁም ውድቀት ለመታደግ የታለመ እንደሆነ ቢቢሲ ፅፏል፡፡

አሜሪካ በዚያው በቬየና ከተደረሰው ስምምነት ለቅቃ ከወጣች 3 ዓመት ሊሆናት ነው፡፡

ይህም ኢራንን ዳግም ለአሜሪካ ማዕቀብ ዳርጓታል፡፡

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አገራቸውን ወደ ስምምነቱ የመመለስ ፍላጎታቸውን ቢያሳውቁም ጉዳዩ ዳግም ድርድር ያሻዋል ባይ ናቸው፡፡

ኢራን ደግሞ አሜሪካ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ወደ ስምምነቱ ተመልሳ ማዕቀቡ እንዲነሳላት እየጠየቀች ነው፡፡

የቬየናው ድርድር ተጀምሯል ቢባልም ኢራን ከአሜሪካውያን ጋር የፊት ለፊት ንግግር አላደርግም እያለች መሆኑ በመረጃው ተጠቅሷል፡፡
 

ቁልፍ ቃላት
ምላሽ