ማስታወቂያ

programs top mid size ad

ጷጉሜ 3፣ 2013- የሜክሲኮ የፓስፊክ ውቅያኖስ ዳርቻ በኃይለኛ ርዕደ መሬት መመታቱ ተሰማ

የሜክሲኮ የፓስፊክ ውቅያኖስ ዳርቻ በኃይለኛ ርዕደ መሬት መመታቱ ተሰማ፡፡የመሬት ነውጡ በርዕደ መሬት መለኪያ (ሬክተር ስኬል) 7 ነጥብ መመዝገቡን ቢቢሲ ፅፏል፡፡

ንቅናቄው በ370 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በምትገኛዋ መዲናዋ ሜክሲኮ ሲቲ ድረስ ተሰምቷል፡፡ርዕደ መሬቱ የተከሰተው በመዝናኛ ስፍራነቱ በምትታወቀው አካፑልኮም ቅርበት እንዳለው ታውቋል፡፡

የኤሌክትሪክ ምስተላለፊያ መውደቅ ምክንያት የአንድ ሰው ሕይወት ማለፉ ታውቋል፡፡ መጠነ ሰፊ የንብረት ውድመት መድረሱ ተነግሯል፡፡

ቁልፍ ቃላት
ምላሽ