ማስታወቂያ

programs top mid size ad

ጷጉሜ 3፣ 2013- የጊኒ ወታደራዊ መሪዎች 80 እስረኞችን መልቀቃቸው ተሰማ

የጊኒ ወታደራዊ መሪዎች 80 እስረኞችን መልቀቃቸው ተሰማ፡፡ የተላቀቁት እስረኞች የእሁድ ዕለቱን የመንግሥት ግልበጣ በመቃወም ለእስር የተደረጉ እንደነበሩ ቢቢሲ አስታውሷል፡፡

የሀገሪቱ የልዩ ኃይል ወታደሮች የፕሬዝዳንት አላፋ ኮንዴን አስተዳደር ማስቀገዳቸው ይታወቃል፡፡ የልዩ ሃይሉ ከፍተኛ የጦር መኮንን ኮሎኔል ማማዲ ዱምቦይ በግልበጣው መሪነት ስማቸው ይነሳል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት፣ የአፍሪካ ህብረት እና የምዕራብ አፍሪካ መንግሥታት ማህበር ኤኮዋስ በየፊናቸው ግልበጣውን አውግዘውታል፡፡ የሀገር ውስጥበ ግን የግልበጣው ጎሽ ባዮች ይበዛሉ፡፡

ፕሬዝዳንት አላፋ ኮንዴ በአወዛጋቢ ምርጫ ለ3ኛ ጊዜ ተመርጠዋል የተባሉት ባለፈው ጥቅምት ወር እንደነበር ለትውስታ ተጠቅሷል፡፡

ቁልፍ ቃላት
ምላሽ