ማስታወቂያ

programs top mid size ad

መስከረም 4፣ 2014- በአፍጋኒስታን መንግስታዊ አስተዳደሩን የተቆጣጠረው ታሊባ ስራ እንዲሰሩ ብፈቅድም ወንድ ሰራተኞች ባሉባቸው ስፍራዎች ድርሽ እንዳይሉ አልፈልግም አለ

በአፍጋኒስታን መንግስታዊ አስተዳደሩን የተቆጣጠረው ታሊባ ስራ እንዲሰሩ ብፈቅድም ወንድ ሰራተኞች ባሉባቸው ስፍራዎች ድርሽ እንዳይሉ አልፈልግም አለ፡፡ 

የአስተዳደሩን አቋም ዕወቁልን ያሉት የታሊባን ከፍተኛ ሹም የሆኑት ዋሂዱላህ ሐሺም እንደሆኑ ሬውተርስ ፅፏል፡፡

በታሊባን አቋም መሰረት ሴቶች በመንግስታዊ ቢሮዎች፣ በባንኮች እና በመገናኛ ብዙኃን ተቋማት የመስራት መብት እንደሌላቸው በመረጃው ተጠቅሷል፡፡

ቀደም ሲል የታሊባኑ የትምህርት ሚኒስትር ሴቶች በዩኒቨርሲቲዎች እና በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እንዲማሩ ብንፈቅድም፤ ወንድ ተማሪዎች ባሉባቸው ተቋማት ድርሽ እንዲሉ አናደርግም ማለታቸውን መረጃው አስታውሷል፡፡ 

በቀዳሚው አስተዳደር ሴቶች በስራም ሆነ በትምህርት ረገድ አንዳችም ገደብ አልነበረባቸውም፡፡

ቁልፍ ቃላት
ምላሽ