ማስታወቂያ

programs top mid size ad

መስከረም 4፣ 2014- የኢትዮ ቴሌኮምን አክሲዮን 40 በመቶ ድርሻ ለመግዛት የፈለገ ማንኛውም ኩባንያ የሐሳብ መጠየቂያ ቅፁን ለማግኘት የማይመለስ 20,000 የአሜሪካ ዶላር ወይም 913,800 ብር መክፈል እንዳለበት የገንዘብ ሚኒስቴር ተናገረ

የኢትዮ ቴሌኮምን አክሲዮን 40 በመቶ ድርሻ ለመግዛት የፈለገ ማንኛውም ኩባንያ የሐሳብ መጠየቂያ ቅፁን ለማግኘት የማይመለስ 20,000 የአሜሪካ ዶላር ወይም 913,800 ብር መክፈል እንዳለበት የገንዘብ ሚኒስቴር ተናገረ፡፡

ሚኒስቴሩ በተጨማሪም ተጫራቾች ምሥጢር የመጠበቅ ግዴታ በመግባት የማረጋገጫ ሰነድ ማቅረብ አለባቸው ብሏል፡፡

የሐሳብ መጠየቂያው (RFP) ድርሻ ለመግዛት ለሚፈልጉ ሁሉ ክፍት መኾኑን ሰምተናል፡፡ 

ጨረታው ከዚህ ቀደም ፍላጎታቸውን ለገለፁ ኩባንያዎች ብቻ የተወሰነ አይደለም ተብሏል፡፡ 

የገንዘብ ሚኒስቴር የመሠረተ ልማት አሥተዳደርና የወደፊት የቴክኖሎጂ አቅሞችን በተመለከተ እሴት መጨመር የሚችሉና ፍላጎት ያላቸው ኩባንያዎች ከኢትዮ ቴሌኮም አክሲዮኖች ውስጥ 40 በመቶ ድርሻ ለመግዛት እንዲወዳደሩ ጋብዟል፡፡ 

ፍላጎት ያላቸው ኩባንያዎች በሙሉ የሐሳበ መጠየቂያ ክፍያውን ገቢ የሚያደርጉበት የባንክ ሒሳብ ዝርዝር መረጃና ምሥጢር ለመጠበቅ የሚገባውን ግዴታ መሙያ ቅጽ ለመውሰድ ከመስከረም 23፣ 2014 ጀምሮ በጽሑፍ ጥያቄ ማቅረብ ይችላሉ ተብሏል፡፡

ቁልፍ ቃላት
ምላሽ