ማስታወቂያ

programs top mid size ad

ህዳር 14፣ 2014- ታሪክን የኋሊት

ታሪክን የኋሊት

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት 767፣ በጠላፊዎች ተገዶ፣ በውቅያኖስ ላይ ከተከሰከሰ ዛሬ 25 ዓመት ሞላው፡፡

በአደጋው ብዙዎቹ ተሳፋሪዎች ሞተዋል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ በበረራ ቁጥር 961፣ 175 ሰዎችን አሳፍሮ ወደ ኬንያ እየበረረ ነበር፡፡

የአይሮፕላኑ አብራሪ፣ በአጠቃላይ 11,500 የበረራ ሰዓት ያስመዘገበውና በቦይንግ 767 አይሮፕላን የ4,067 የበረራ ሰዓት ያስመዘገበ ነባር አብራሪ ነው፡፡

አይሮፕላኑ 20 ደቂቃ ከበረራና ከፍታውን እንደያዘ ከጧቱ 2፡29 ደቂቃ ሁለት ጠላፊዎች በአብሪዎቹ ክፍል ገብተው አይሮፕላኑ መጠለፉንና አቅጣጫውን ወደ አውስትራሊያ እንዲያደርግ ካፒቴን ልዑልን አዘዙት፡፡

ካለበለዚያ በቦምብ አይሮፕላኑን እንደሚያጋዩት ነገሩት፡፡

ጠላፊዎቹ 3 ሲሆኑ ሁለቱ ሥራ የሌላቸውና አንደኛው ነርስ እንደሆነ በኋላ ተነግሩዋል፡፡
ጠላፊዎቹ ቦምብ አስመስለው የያዙት መጠጥ የያዘ ጠርሙስ እንደነበረ በኋላ ተረጋግጧል፡፡

ጠላፊዎቹ ረዳት አብራሪውን ዮናስ መኩሪያን አስገድደው ከክፍሉ ካስወጡ በኋላ  አይሮፕላኑ መጠለፉን በአማርኛና በእንግሊዘኛ ቋንቋዎች ተናገሩ፡፡

ማንም ቢንቀሳቀስ  በቦምብ እንደሚያጋዩት አስፈራሩ፡፡

ካፒቴኑ  ያለው ነዳጅ ሊያደርሰው የሚችለው ናይሮቢ ብቻ መሆኑን ሊያስረዳቸው ሞከረ፤ አልተቀበሉትም፡፡

ካፒቴን ልዑል ወደ አውስትራሊያ መብረሩን ትቶ ወደ ደቡብ በኩል አቅጣጫውን ወደ ኮሞሮስ አደረገ፡፡

አይሮፕላኑ ነዳጅ እያለቀበት ነበር ጠላፊዎቹ ግን ማስጠንቀቂያውን ለመስማት አልፈለጉም፡፡

አንደኛው ጠላፊ ከጓደኞቹ ጋር ለመነጋገር ከአጠገቡ ዘወር ሲልለት ካፒቴን ልዑል አጋጣሚውን ተጠቅሞ ለተጓዞቹ መልዕክት አስተላለፈ፡፡

“ነዳጅ እየጨረስን ነው፤ አንደኛው ሞተር ጠፍቷል፤ የምላችሁ ይኽንኑ ነው፤ ስለዚህ ተጓዦች ጠላፊዎቹን አንድ ነገር እንድታረጉ እጠይቃለሁ፡፡” አለ፡፡
ይህን ንግግር ሲሰማ ጠላፊው ተመልሶ መናገሪያው ነጠቀው ወዲያው የግራ ክንፉ መቀጣጠል ጀመረ፡፡

ሁለቱም ሞተሮች መቃጠል ጀመሩ፡፡

ካፒቴን ልዑል የአደጋ ጊዜ በሚደረግ የማረፍ ስልት በኮሞሮስ የአይሮፕላን ጣቢያ ለማረፍ ፈለገ፡፡

ግን አይሮፕላኑ እየወዛዠቀ ሜዳውን ለመለየት አዳገተው፤ ስለዚህ 460 ሜትር ጥልቀት ባለው ባህር ላይ ለማሳረፍ ሞከረ፡፡

አይሮፕላኑ ከውቅያኖስ ላይ ሲያርፍ ለሁለት ተከፈለ፤ አንደኛው ክፍል ጠለቀ፡፡

ተጓዦቹም በምቱና በውሃው ጥልቀት ተጎዱ፡፡

ሶስቱ ጠላፊዎች ጨምሮ 125 የሚሆኑት ተሳፋሪዎችና የበረራ ቡድኑ አባላት ሞቱ፡፡ 

ከሟቾቹ መካከል የኢትዮጵያ ወዳጅ የነበረውና ዓለም አቀፍ እውቅና የነበረው ጋዜጠኛ መሐመድ አሊ ይገኝበታል፡፡

ካፒቴን ልዑልንና ረዳት አብራሪውን ፣ ስድስት የበረራ ቡድን አባላቱን ጨምሮ 50 ተጓዦች ከአደጋው ተረፉ፡፡

ይህ ከሆነ ዛሬ 25 ዓመት ሞላው፡፡

ቁልፍ ቃላት
ምላሽ