ማስታወቂያ

programs top mid size ad

ጥር 6፣ 2014- ሕብረት ባንክ ወርቅ፣ አልማዝ እና ሌሎች ውድ እቃዎች እንዲሁም በጥንቃቄ መያዝ ያለባቸው ዶክመንቶች የሚቀመጡበት እጅግ ዘመናዊ ቅርንጫፍ በመክፈት አዲስ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ተናገረ

Image
ሕብረት ባንክ

ሕብረት ባንክ ወርቅ፣ አልማዝ እና ሌሎች ውድ እቃዎች እንዲሁም በጥንቃቄ መያዝ ያለባቸው ዶክመንቶች የሚቀመጡበት እጅግ ዘመናዊ ቅርንጫፍ በመክፈት አዲስ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ተናገረ፡፡ 

ውድ እቃዎችና ዶክመንቶች በአደራ የሚቀመጥበት ቅርንጫፍ የሚገኘው በዋና መስሪያ ቤቱ ህብር ህንፃ ስር መሆኑን ሰምተናል፡፡

ባንኩ ከዚህ በፊት ለዋና መስሪያ ቤት በየወሩ 1.5 ሚሊዮን ኪራይ እከፍል ነበር ብሏል፡፡

ይህንንም የሚያስቀርልኝን ህንፃ በ2.7 ቢሊየን ወጭ ገንብቼ ነገ አስመርቀዋለሁ ማለቱን ሰምተናል፡፡

ግንባታው 6 ዓመት ፈጅቷል፡፡

የሕብረት ባንክ ዋና መስሪያ ቤት ባለ 37 ወለል መሆኑን የባንኩ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መላኩ ከበደ ሲናገሩ ሰምተናል፡፡

ዋና መስሪያ ቤቱ በማይጨው አደባባይ አካባቢ የፋይናንስ ተቋሞ አጥቢያ ይገኛል፡፡ የህንፃው ስያሜ ህብር ታወር ተብሏል፡፡

ሕብረት ባንክ አለም የደረሰባቸው አገልግሎቶችና በዘመናዊ ኮምፓስ የሚሰሩ 13 ዲጂታል አሳንሰሮች ተገጥመውለታል፡፡

ህንፃው የማይቋረጥ የሀይል አቅርቦት Building management system አለው ተብሏል፡፡

ቁልፍ ቃላት
ምላሽ