ማስታወቂያ

programs top mid size ad

ታህሳስ 16፣2012/ የሸገር ስፖርት ወሬዎች-የቦክሲንግ ደይ የጨዋታ መርሃግብሮች ቅድመ ዳሰሳ(PL Boxing day matches preview)

የቦክሲንግ ደይ የጨዋታ መርሃግብሮች ቅድመ ዳሰሳ(PL Boxing day matches preview)

ዐቢይ ነጥቦች፡
በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ አንደኛ እና ሁለተኛ ላይ የሚገኙት ሊቨርፑልና ሌስተር ሲቲ ምሽት 5 ሰዓት ላይ የሚያደርጉት ጨዋታ ከወዲሁ ልዩ ትኩረት አግኝቷል፣ በርካታ ሃሳቦችም እየተሰነዘሩ ይገኛሉ።ሁለቱ የቅርብ ተሿሚዎች፣ የአርሰናሉ ሚኬል አርቴታ እና የኤቨርተኑ ካርሎ አንችሎቲ ክለቦቻቸውን እየመሩ የሚያደርጓቸው ጨዋታዎች ሌሎቹ የትኩረት አቅጣጫዎች ናቸው።የሊጉ መሪ ሊቨርፑል ከዓለም የክለቦች ዋንጫ አሸናፊነት ማግስት ወደ ኪንግ ፓወር ተጉዘው ምርጡ ሌስተር ሲቲን ይገጥማሉ።
ባሳለፍነው ሳምንት በቼልሲ በአሳማኝ ሁኔታ ሁለት ለዜሮ የተሸነፉት ቶተንሃሞች በሜዳቸው ብራይተን ኤንድ ኦቭ አልቢዮንን ያስተናግዳሉ።

ዦዜ ሞሪንሆ በቀድሞ ተጫዋቻቸው ፍራንክ ላምፓርድ ብልጫ ባለው ታክቲክ ከደረሰባቸው ሽንፈት ለማገገም የዛሬውን ጨዋታ ማሸነፍ ይኖርባቸዋል።በአጠቃላይ የሰሞኑን ጨዋታዎች ማሸነፍ የሚችሉ ቡድኖች ድሎቻቸው እንደ ጥሩ የገና ስጦታ ሊኾኑሏቸው ይችላሉ።

ተጨማሪ ሃሳቦች፡

የበዓላት ሰሞን፣በብርታኒያ ምድር ከሚደረጉ ጨዋታዎች በቀር በርካታ የአውሮፓ ሊጎች ዝግ ናቸው።የብርታኒያ እግር ኳስ ግን ወቅቱን የውድድር ካሌንደሩን ለማፍጠን ይጠቀምበታል።በ3 ቀናት ውስጥ 2 የጨዋታ መርሃግብሮች (የ19ኛ እና 20ኛ ሳምንት) ስለሚያደርጉ ሊጋቸውን ከሌሎቹ የአውሮፓ አቻዎቻቸው ከ2 ሳምንታት በፊት ያጠናቅቃሉ።ምንም እንኳን ሊጉን በጊዜ ከማጠናቀቅ አኳያ ጥቅም ቢኖረውም ከጨዋታ በኋላ የተጫዋቾች የማገገሚያ ሰዓት እና ሁኔታ (recovery time and situation) ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ያሳድራል።
 
የጨዋታ መርሃ ግብሮች

ቀን 9:30
ቶተንሃም ከ ብራይተን
አመሻሽ 12:00
ኤቨርተን ከ በርንሌይ
ክሪስታል ፓላስ ከ ዌስትሃም
ቼልሲ ከ ሳውዝሃምፕተን
ሼፊልድ ዩናይትድ ከ ዋትፎርድ
በርንማውዝ ከ አርሰናል
አሰሰቶን ቪላ ከኖርዊች ሲቲ
ምሽት 2:30
ማን ዩናይትድ ከ ኒውካስትል
ምሽት 5:00
ሌስተር ሲቲ ከ ሊቨርፑል

ዐቢይ ሐብታሙ
ቁልፍ ቃላት
ምላሽ