ማስታወቂያ

programs top mid size ad

ታህሳስ 15፣2012/ የሸገር ስፖርት ወሬዎች-የዓለም የክለቦች ሻምፒዮና የኾኑት ሊቨርፑሎች...

የዓለም የክለቦች ሻምፒዮና የኾኑት ሊቨርፑሎች በአንድ የፕሪምየር ሊግ ጨዋታ ላይ ብቻ ወርቃማውን ባጅ ለብሰው እንዲጫወቱ ይኹንታን ማግኘታቸውን ዘ ቴሌግራፍ ተናግሯል።
ሁነኛ አሰልጣኝ በማፈላለግ ላይ የሚገኙት የፈረንሳዩ ክለብ ሞናኮ ኃላፊዎች ዐይናቸውን ወደ ቀድሞው የአርሰናል አሰልጣኝ ስፔናዊው ኡናይ ኤምሬ እያማተሩ ናቸው ተብሏል።የባስኩ ሰው የመድፈኞቹን ቤት ከተሰናበቱ ወዲህ ከሥራ ወጪ መኾናቸው ይታወቃል። የስፔኑ የወሬ ምንጭ አስ ባወጣው መረጃ ደግሞ ኤምሬ በሞናኮ የአሰልጣኝነት ህይወት አልሰምርልህ ያለውን ሊዮናርዶ ዣርዲምን ምናልባት ሊተኩ ይችላሉ ብሏል።
የአርሰናሉ ወጣት ተጫዋች ቡካዮ ሳካ ለየትኛው ብሔራዊ ቡድን መጫወት እንዳለበት አስካሁን አለመወሰኑ ተሰምቷል።እንደ ዘ ሰን ዘገባ ከኾነ ይህ የ18 ዓመት የክንፍ ተጫዋች የእንግሊዝ ዜግነት ቢኖረውም ለምዕራብ አፍሪካዊቷ አገር ናይጄሪያ ብሔራዊ ቡድን የመጫወት እድል አለው ተብሏል።

ዐቢይ ሐብታሙ
ቁልፍ ቃላት
ምላሽ