ማስታወቂያ

programs top mid size ad

ታህሳስ 21፣2012/ የሸገር ስፖርት ወሬዎች- ሞሮኳዊው አብድረዛቅ ሃምዳላህ የ2019 የዓለማችን ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ሆኗል

ሞሮኳዊው አብድረዛቅ ሃምዳላህ የ2019 የዓለማችን ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ሆኗል።ሃምዳላህ የሳውዲ ሊግ ክለብ የኾነው አል ናስር ተጫዋች ነው።ባሳለፍነው ቅዳሜ አል ፊያህ ላይ ባስቆጠራቸው 3 ጎሎች ወደ ዓለማችን ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነት ተሸጋግሯል።
ተጫዋቹ 57 ጎሎችን በማስቆጠር እንደ ሮበርት ሌቫንዶቭስኪና ሊዮ ሜሲ ያሉ ከዋክብቶችን በመብለጥ የ2019 ውድድር ዘመን ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነት ክብርን አግኝቷል።
ኤሪክ ቤይ ወደ ጨዋታ ሊመለስ ተቃርቧል።ቤይ ጉልበቱ ላይ ከተደረገለት ቀዶ ጥገና በኃላ ማገገም በመቻሉ በቅርብ ጊዜ ወስጥ ለጨዋታ ዝግጁ ይሆናል ተብሏል።ትናንት የመጀመሪያ ልምምዱን ማድረጉም ተሰምቷል።ይህ ኮትዲቫራዊ ተጫዋች ለክለቡ በሁሉም ውድድሮች የተሳተፈባቸው የጨዋታ ብዛት 7 ብቻ ነበሩ።
ካሪም ቤንዜማ ከሪያል ማድሪድ ጋር ያለውን የውል ስምምነት አሯዝሟል።ቤንዜማ ውሉን ያደሰው ለተጨማሪ 1 ዓመት ነው።አዲሱ የውል ስምምነት ተጫዋቹን በሎስ ብላንኮዎቹ ቤት እስከ 2022 የውድድር ዘመን ድረስ ያከርመዋል።የቤንዜማ የቀደመ የውል ስምምነት እስከ 2021 ድረስ የሚዘልቅ ነበር።

ዐቢይ ሐብታሙ
ቁልፍ ቃላት
ምላሽ