ቢዝነስ ወሬ

ህዳር 24፣ 2014- አሁን በኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሬ መያዝ ባለበት ጊዜ በከተማው ግን ከ1.5 እስከ 20 ሚሊየን ብር የሚሸጡ መኪናዎች ደረታቸውን ገልብጠው የሚዛቸውን ኢትዮጵያዊ ይጠብቃሉ

አሁን በኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሬ መያዝ ባለበት ጊዜ በከተማው ግን ከ1.5 እስከ 20 ሚሊየን ብር የሚሸጡ መኪናዎች ደረታቸውን ገልብጠው የሚዛቸውን ኢትዮጵያዊ ይጠብቃሉ፡፡ 

ሻፓኙም፣ ውስኪውም እንደ ልብ ይጨለጣል፡፡ 

ይህ ምን ይነግረናል? 

ምላሽ

መስከረም 20፣ 2014- በዛሬው የገበያ ቅኝት መሰናዶዓችን በአዲስ አበባ ከተማ በስፋት እየተለመደ የመጣውን የእሁድ ገበያ እንቃኛለን

በዛሬው የገበያ ቅኝት መሰናዶዓችን በአዲስ አበባ ከተማ በስፋት እየተለመደ የመጣውን የእሁድ ገበያ እንቃኛለን፡፡ 

በቀደሙት ዓመታት በአብዛኛው አልባሳት ብቻ ይሸጡባቸው የነበሩት የእሁድ ገበያዎች አሁን አሁን ለገበያ የሚቀርቡት ሸቀጦች በዓይነትም እየሰፉ መኾኑን ሸገር ተመልክቷል፡፡ 

ምላሽ

ህዳር 22፣2014/ ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ ከነገ ጀምሮ መጠሪያውን ወደ ኦሮሚያ ባንክ እንደሚቀይር ተሰማ

ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ ከነገ ጀምሮ መጠሪያውን ወደ ኦሮሚያ ባንክ እንደሚቀይር ተሰማ።

ባንኩ ከእንግዲህ በኋላ “ኦሮሚያ ባንክ’’ ተብሎ እንደሚጠራ ሸገር ከምንጮቹ ሰምቷል፡፡ 

ባንኩ ለ13 ዓመት የተጠቀምኩበትን የንግድ ምልክት ከዘመኑ ጋር በሚጓዝ መልኩ እቀይራለሁ  ብሏል።

የባንኩ ፕሬዝዳንት አቶ ተፈሪ መኮንን የባንኩን አዲስ የንግድ ምልክት በነገው ዕለት እናስተዋውቃለን ሲሉ ተናግረዋል። 

ተቋማዊ የንግድ ስያሜና መለያውን ለመለወጥ የ20 ወራት ጊዜ እንደፈጀ ፕሬዝዳንቱ ሲናገሩ ሰምተናል።

ምላሽ

ህዳር 22፣ 2014/ ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ዘመኑ የደረሰበትን የባንክ ቴክኖሎጂ መጠቀም ጀመርኩ አለ

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ዘመኑ የደረሰበትን የባንክ ቴክኖሎጂ መጠቀም ጀመርኩ አለ፡፡

ባንኩ T 24 R 2020 በመባል የሚጠራውን ቴክኖሎጂ ዘርግቶ መጠቀም መጀመሩን ዛሬ በሰጠው መግለጫ ተናግሯል፡፡

የባንኩ ፕሬዝዳንት አቶ ገነነ ሩጋ፣ ባንከቸው ቴክኖሎጂውን ከሌሎች ኢትዮጲያ ውስጥ ካሉ ባንኮች ቀድሞ መጀመሩን ተናግረዋል፡፡

ቴክኖሎጂው የባንኩን ሥራ ቀልጣፋ፣ ዘመናዊ እና ምቹ ለማድረግ በብርቱ ያግዛል ተብሏል፡፡

ባንኩ አዲስ ባቀረብኩት ቴክኖሎጂ የሞባይልና የኢንተርኔት ባንኪንግ አገልግሎቴን በከፍተኛ ሁኔታ የቀለጠፈና የማያስቸግር ለማድረግ ያስችለኛል ብሏል፡፡

ምላሽ
ወሬ መለያዎች
Reset filters
2021-12-04
መሠረታዊ የሚባሉና ዜጎችን የሚጠቅሙ የጤና መረጃዎች በነፃ የሚቀርቡበት ማዕከል ዛሬ ሥራ መጀመሩ ተነገረ፡፡  በማዕከሉ…
2021-12-04
መሠረታዊ የሚባሉና ዜጎችን የሚጠቅሙ የጤና መረጃዎች በነፃ የሚቀርቡበት ማዕከል ዛሬ ሥራ መጀመሩ ተነገረ፡፡  በማዕከሉ…
2021-12-04
ሕወሃት በአፋር ክልል የተፈፀመው ወረራ ባደረሰው ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ቀውስ ሳቢያ በክልሉ ከ1.3 ሚሊዮን በላይ የሚሆን…
2021-12-04
በመካከለኛው ምስራቅ ቀጠና በእስራኤል እና በኢራን መካከል ያለው ግንኙነት ፍፁም የጠላትነት ነው፡፡ በኢራን የኒኩሊየር መርሃ…
2021-12-04
ኢትዮጵያ በህግ አውጪ አካሏ ሽብርተኛ ብላ የፈረጀችውን ሕወሃት መዋጋት ከጀመረች 1 ዓመት አልፏታል፡፡ ጦርነቱ፣ ውጊያው…
2021-12-04
ኢትዮጵያ በህግ አውጪ አካሏ ሽብርተኛ ብላ የፈረጀችውን ሕወሃት መዋጋት ከጀመረች 1 ዓመት አልፏታል፡፡ ጦርነቱ፣ ውጊያው…