top of page


በቀይ ባህር ደኅንነት ላይ ረጅም ስትራቴጂካዊ ታሪክ ያላትን ኢትዮጵያን ያገለለው የቀይ ባህር ደኅንነት ኅብረት፣ በኢትዮጵያ ጂኦፖለቲካዊ ሁኔታ ላይ ምን ዓይነት ተፅዕኖ ይኖረዋል?
ነሐሴ 14 2018 በቀይ ባህር ደኅንነት ላይ ረጅም ስትራቴጂካዊ ታሪክ ያላትን ኢትዮጵያን ያገለለው የቀይ ባህር ደኅንነት ኅብረት፣ በኢትዮጵያ ጂኦፖለቲካዊ ሁኔታ ላይ ምን ዓይነት ተፅዕኖ ይኖረዋል? ሰሞኑን ሳውዲ ዓረብያ፣ ቱርክ፣ ግብፅ፣ ሶማሊያ፣ ሱዳን፣ ጅቡቲ እና ሌሎች ከ13 በላይ የሚሆኑ ሀገራት የቀይ ባህር እና የኤደን ባህረ ሰላጤ ደኅንነት ትብብርን መስርተዋል። በቀይ ባህር እና አጎራባች አካባቢዎች ያለውን የባህር ላይ እንቅስቃሴ ደኅንነት ለመጠበቅ ያለመ ነው የተባለለት ይህ ኅብረት፣ በቀይ ባህር ደኅንነት ላይ የረጅም ጊዜ ስትራቴጂያዊ ተሳትፎ የነበራትን ኢትዮጵያን አላካተተም። በዋቻሞ ዩኒቨርሲቲ የዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህሩ ሙሉዓለም ኃይለማርያም፣ ይህ ኅብረት ኢትዮጵያን በጂኦፖለቲካዊ ከበባ ውስጥ እንዳያስገባት መጠንቀቅ ያስፈልጋል ይላሉ። እ
1 minute ago
ከሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ ውይይት ሲካሄድባቸው ለቆዩ 8 ዋና ዋና አጀንዳዎች እና 96 ንዑስ አጀንዳዎች 476 የምክረ ሐሳብ ነጥቦች ለ4 ሺህ ጉባኤተኞች ዛሬ ቀርበዋል።
ነሐሴ 13 2018 ከሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ ውይይት ሲካሄድባቸው ለቆዩ 8 ዋና ዋና አጀንዳዎች እና 96 ንዑስ አጀንዳዎች 476 የምክረ ሐሳብ ነጥቦች ለ4 ሺህ ጉባኤተኞች ዛሬ ቀርበዋል። በዚህም መሠረት ለመንግሥት አደረጃጀት እና ቅርጽ አጀንዳ የሚከተሉት የምክረ ሐሳብ ነጥቦች ተሰጥተዋል፦ · የፌደራሊዝም ሥርዓት፦ የፌደራሊዝም ሥርዓቱ እንዲቀጥል ተስማምተዋል። · የመንግሥት ቅርጽ፦ የመንግሥት ቅርጽ ከፓርላሜንታዊ ሥርዓት እንዲቀጥል፤ ነገር ግን የአገሪቱ ርዕሰ ብሔርም፣ ርዕሰ መንግሥትም ሆኖ የሚያገለግል ፕሬዚዳንት ከፓርላማ ይመረጥ የሚለው ሐሳብ በአብዛኞቹ ተመካካሪዎች ተደግፏል። · የሥራ ዘመን ገደብ፦ የክልልም ሆነ የፌደራል መንግሥት የሥራ ዘመን በየ6 ዓመቱ በሚካሄድ ምርጫ በሁለት የሥራ ዘመን ብቻ የ
5 hours ago


ህገ መንግስቱ መሻሻል የሚችለው ሁሉም የክልል ምክር ቤቶች የቀረበውን ማሻሻያ በአብላጫ ድምጽ ሲያጸድቁት ነው የሚለው የህገ መንግስቱ ድንጋጌ ቀርቶ፣ ሶስት አራተኛ የክልል ምክር ቤቶች ሲያጸድቁት በሚለው እንዲተካ ለመጨረሻ የቀረበው የምክረ ሃሳብ ሰነድ ያስረዳል፡፡
ነሐሴ 13 2018 ህገ መንግስቱ መሻሻል የሚችለው ሁሉም የክልል ምክር ቤቶች የቀረበውን ማሻሻያ በአብላጫ ድምጽ ሲያጸድቁት ነው የሚለው የህገ መንግስቱ ድንጋጌ ቀርቶ፣ ሶስት አራተኛ የክልል ምክር ቤቶች ሲያጸድቁት በሚለው እንዲተካ ለመጨረሻ የቀረበው የምክረ ሃሳብ ሰነድ ያስረዳል፡፡ የሽግግር ፍትህ የህግ ተጠያቂነት ከ1987 ዓ.ም ጀምሮ እንዲሆን የተዘጋጁ ህጎች እንዲጸድቁ፣ የሚቋቋሙ ተቋማትም እንዲለዩ እና በአፋጣኝ ወደ ስራ እንዲገቡ ምክረ ሃሳብ ቀርቧል። "የመንግስት አደረጃጀት እና ቅርጽ" በሚለው ዋና አጀንዳ ስር የመከረው ቡድን ፓርላሜንታዊ ስርዓት እንዲቀጥል ተስማምቷል፤ ነገር ግን አገሪቱን ርዕሰ ብሔርም፣ ርዕሰ መንግስትም ሆኖ የሚመራት ፕሬዚዳንት ይሁን፤ እሱም ከፓርላማ ይመረጥ የሚለውን ምክረ ሃሳብ "በአብዛኛው" ሲል በገለጸው ተሳታፊ መደገፉን
6 hours ago
የኤልኒኖ የአየር ንብረት ለውጥ ክስተት በክረምቱ ዝናብ ላይ እጥረት እያስከተለ መሆኑ ይታያል፡፡
ነሐሴ 13 2018 የኤልኒኖ የአየር ንብረት ለውጥ ክስተት በክረምቱ ዝናብ ላይ እጥረት እያስከተለ መሆኑ ይታያል፡፡ ይህ መሆኑ ከምታመርተው የኤልክትሪክ ሃይል 97 በመቶውን ከውሃ የምታመርተው ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጡን ለመቋቋም ምን እየሰራች ነው? የዝናብ እጥረቱ እስከ መስከረም መጨረሻ ድረስ ከቀጠለ ለውጭ ሃገራት የሚሸጠውን የኤሌክትሪክ ሃይል ከመቀነስ ጀምሮ የተለያዩ እርምጃዎች ይወሰዳሉ ተብሏል፡፡ ዘንድሮ በምስራቅ አፍሪካ የተከሰተው የኤልኒኖ የአየር ንብረት ለውጥ ክስተት የክረምቱ የዝናብ መጠን ከመደበኛው በታች እንዲሆን አድርጎታል፤ በዚህም ምክንያት በተለይ ሃይል ማመንጫ ግድቦች ውሃን የመያዝ አቅም ሊቀንሰው ይችላል ሲል የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ትንበያውን መስጠቱ ይታወሳል። ከአፍሪካ በግዝፈቱ ቀዳሚ የሆነው የህዳሴ ግድብ የውሃ
6 hours ago
አከራካሪ ሆኖ የቆየውን የአዲስ አበባ ጉዳይን ጨምሮ ለ8ቱም አጀንዳዎች የተሰጡ የመጨረሻ ምክረ ሀሳቦች ለ4 ሺህ ጉባዔኞች ቀረቡ።
ነሐሴ 13 2018 አከራካሪ ሆኖ የቆየውን የአዲስ አበባ ጉዳይን ጨምሮ ለ8ቱም አጀንዳዎች የተሰጡ የመጨረሻ ምክረ ሀሳቦች ለ4 ሺህ ጉባዔኞች ቀረቡ። ዛሬ ነሐሴ 13 ቀን 2018 ዓ.ም ለ8 አጀንዳዎች፣ ለ96 ንዑሳን አጀንዳዎች እና ለ225 መሪ ጥያቄዎች 476 ምክረ ሀሳቦች ቀርበዋል። በዚህም በፌደራል ከተሞች አጀንዳ ስር ሲያከራክር ለቆየው የአዲስ አበባ እና ድሬዳዋ ከተሞች ባለቤትነት ጉዳይ የተሰጡ ምክረ ሀሳቦች ዛሬ ለጉባዔተኛው ተነበዋል። አዲስ አበባ የፌደራል መንግስት አካል ትሁን፤ ራሷን በራሷ ታስተዳድር የሚለው አንደኛው አማራጭ ነው። የኦሮሚያ ክልል ከአዲስ አበባ "ልዩ ጥቅም" የሚለው ቀርቶ "የጋራ ጥቅም" በሚል ይስተካከል የሚለው ሌላኛው ምክረ ሀሳብ ሆኖ ሰፍሯል። አዲስ አበባ የኦሮሚያ መቀመጫ መሆኗን በተመለከተ ደግሞ ሁለት ምክረ ሀሳቦች ተቀ
23 hours ago












bottom of page
_edited.jpg)








