ማስታወቂያ

የሸገር ወሬዎቻችን

Sort by
ነባሪ
Post Date
2021-05-15
የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር የ29 ኩባንያዎችን ፈቃድ ሊነጥቅ ነው፡፡  መስሪያ ቤቱ ወደ ምርት ያልገቡ የማዕድን ኩባንያዎች ሁሉም ስራ እንዲጀምሩ ብርቱ ጥረት ላይ ነኝ ብለዋል በነዚህና በሌሎች ጉዳዮች መግለጫም ሰጥቷል፡፡   
2021-05-15
የመርካቶ ዘመናዊ የከተማ አውቶብስ ተርሚናል ዛሬ ተመረቀ፡፡  በ200 ሚሊየን ብር የተገነባው የአውቶብስ ተርሚናል በአንድ ጊዜ ለ20 አውቶብሶች አገልግሎት መስጠት ያስችላል ተብሏል፡፡ ተርሚናሉ የራሳቸው መግቢያ መውጫ ያላቸው 2 ወለሎች አሉት፡፡ 35 የሚሆኑ የአንበሳ የከተማ አውቶብስ ድርጅት መስመሮችና 17 የሚሆኑ የሸገር የብዙሃን ትራንስፖርት ድርጅት መስመሮች አገልግሎት ያገኙበታልም ተብሏል፡፡ በሰዓት ከ6000 በላይ በቀን ደግሞ ከ80,000 በላይ የብዙሃን ትራንስፖርት ተጠቃሚ ደንበኞች አገልግሎት የሚያገኙበት ተርሚናል ይሆናል ተብሎ እንደሚጠበቅ የአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬተሪያት ቢሮ ተናግረዋል፡፡  
2021-05-15
በመጭው ግንቦት 28 ለሚካሄደው 6ኛው ሃገራዊ ምርጫ የሚሆኑ የድምፅ መስጫ ወረቀቶች በደቡብ አፍሪካና በዱባይ እየታተሙ ነው፡፡ ህትመቱ ያለበትን ሁኔታ በተመለከተ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከዓለም አቀፍ የልማት ድርጅት (UNDP) ጋር በመተባበር ጉዳዩ የሚያገባቸውን አካላት አስገብኝቷል፡፡ በደቡብ አፍሪካው የሬን ፎርም ማተሚያ ሶሊውሽኝ እየታተመ ያለው የመራጮች የድምፅ መስጫ የወረቀት ህትመት ሂደት ጉብኝትን የታደመው ባልደረባችን የኔነህ ሲሳይ ይህን ይዞ ተመልሷል፡፡  
2021-05-15
ፓርቲዎች የመራጮችን ድምፅ በማግኘት አሸናፊ ያደርገናል ያሉትን አማራጭ ሀሳብ በዝርዝር ለህዝብ ከማሳወቅ ይልቅ እየተካሄደ ባለው የምረጡኝ ቅስቀሳ አንዱ ሌላውን መወንጀልና መነቋቆር እንዳበዙ ብዙዎች ትዝብታቸውን እየተናገሩ ነው፡፡  ይህም ፓርቲዎች ራሳቸው እንተዳደርበታለን ብለው በጋራ የፈረሙትን የቃል ኪዳን ሰነድ የጣሰ ነው፡፡ እንዲህ ያለው ነገር ምርጫው ሰላማዊ እንዳይሆን አያደርግም ወይ? እንዴትስ ይታረም? 
2021-05-15
ሲሚንቶን በተመለከተ መንግሥት በግብይት ሰንሰለቱ የተሰገሰገውን ደላላ አስወጣለሁ፣ ገበያውን አረጋጋለሁ ብሎ አዲስ  አሰራር ዘርግቷል፡፡  የትኛውም የሲሚንቶ ተጠቃሚ የንግድ ፈቃዱን እያሳየ መንግሥት በተመነለት ዋጋ እና ይበቃሃል ያለውን መጠን ከተፈቀደላቸው ቸርቻሪዎች ይግዛ ብሏል፡፡ ይህ አሰራር ግን በተለይ ትላልቅ ግንባታ እየሰሩ ያሉ የስራ ተቋራጮችን እግር ከወረች አስሮናል ይላሉ፡፡ በተለያየ ቦታ እስከ 12 ወለል ፎቅ እየገነባ ላለ የስራ ተቋራጭ በ5 ቀን አንዴ በሚሰጠው 20 ኩንታል ሲሚንቶ ምን ሊሰራለት ይችላል? ሲሉም ይጠይቃሉ፡፡
2021-05-15
ሳምንታት በቀረው ሃገራዊ ምርጫ ላይ የሚሳተፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች በተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን የምረጡኝ ቅስቀሳ ማድረግ ከጀመሩ ሰነባብተዋል፤ ክርክርም እያደረጉ ነው፡፡ ለመሆኑ መራጩ ሕዝብ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ክርክር በተመለከተ ምን ይላል?  የፓርቲዎች ክርክር ወቅታዊ የኢትዮጵያ ችግሮችን ያገናዘበና አማራጭ ፖሊሲዎችን የሚያሳይ ነው ወይ? 
2021-05-14
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና በባለሀብቶች ትብብር ‘አሙዲን’ የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል በሚል ስያሜ ተመርቆ ተከፍቷል፡፡  
2021-05-14
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና በባለሀብቶች ትብብር ‘አሙዲን’ የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል በሚል ስያሜ ተመርቆ ተከፍቷል፡፡  
2021-05-14
የአዲስ አበባ የትራንስፖርት ቢሮ ያስገነባው የመርካቶ የከተማ አውቶቡስ ተርሚናል ግንባታው ተጠናቆ ነገ ይመረቃል ተባለ። ተርሚናሉ በድጋሚ በዘመናዊ መንገድ ተገንብቶ አገልግሎት እንዲሰጥ ላለፉት ጊዜያት ሙሉ በሙሉ እድሳት ላይ ቆይቷል ተብሏል፡፡ በ4,125 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈው የመርካቶ የአውቶቡስ ተርሚናል በባለሁለት ወለሎች ለ20 አውቶቡሶች አገልግሎት እንደሚሰጥ ከአዲስ አበባ የትራንስፖርት ቢሮ ሰምተናል፡፡ ሁለቱ ወለሎች የራሳቸው መግቢያ እና መውጫ የተገነባላቸው መሆናቸው ተነግሯል፡፡ ተርሚናሉ በሰዓት ውስጥ 6000 ለሚጠጉ ተጓዦች አገልግሎት እንዲሰጥ ታስቦ የተገነባ ነው ተብሏል፡፡ የአውቶቡስ መጠበቂያ ቦታ፣ የትኬት ሽያጭ፤ የተሳፋሪ መጫኛና የማራገፊያ ቦታ፤ ዘመናዊ የስምሪት አገልግሎት፣ የአውቶቡስ መርሃ-ግብር እና የአስተዳደር ቢሮዎችን ማካተቱ የተነገረለት የመርካቶ ዘመናዊ ተርሚናል 200 ሚሊዮን ብር ወጪ ተደርጎበታል ተብሏል፡፡ የግንባታ ወጪውም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተሸፈነ እንደሆነ ሰምተናል፡፡  
2021-05-14
በአዲስ አበባ ከደረቅ ቆሻሻ  ሽያጭ 432 ሚሊየን ብር መገኘቱ ተነገረ፡፡ በዚሁ ጊዜ እንደተባለው ባለፉት 9ወራት በደረቅ ቆሻሻ መልሶ መጠቀምና ኡደት ለ3,088 ያህል ወጣቶችና ሴቶች የስራ እድል ለመፍጠር ተችሏል፡፡  ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደረቅ ቆሻሻ አስተዳደር ኤጀንሲ  እንደሰማነው 36,280 ቶን የኮምፓስት፣ ወረቀትና ካርቶን  እንዲሁም ፕላስቲክ ጠርሙስ ምርት መሰብሰብ ተችሏል፡፡  የተገኘውን የደረቅ ቆሻሻ ምርት ለአገር ውስጥና ለውጭ ገበያ  በማቅረብ ከ432 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መገኘቱን የአዲስ  አበባ ፕሬስ ስክሬታሪያትመረጃ ያሳያል፡፡ ይህንኑ የደረቅ ቆሻሻ መልሶ መጠቀምና ኡደት ስራን የሚያሳይ ኤግዚቢሽን በሚኒልክ አደባባይ በዛሬው እለት ለእይታ ክፍት መደረጉን ሰምተናል፡፡