ማስታወቂያ

programs top mid size ad

ሚያዝያ 15፣ 2013- የኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ባለፉት 7 ዓመታት በፀጥታ መደፍረስ፣ በዋጋ ንረት እና በግብዓት እጥረት ሲፈተን መቆየቱን የከተማ ልማት እና ኮንስትራሽን ሚኒስትሯ ተናገሩ

የኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ባለፉት 7 ዓመታት በፀጥታ መደፍረስ፣ በዋጋ ንረት እና በግብዓት እጥረት ሲፈተን መቆየቱን የከተማ ልማት እና ኮንስትራሽን ሚኒስትሯ ተናገሩ፡፡

ሚኒስትሯ ኢንጂኒየር አይሻ መሐመድ በስካይ ላይት ሆቴል በመካሄድ ላይ በሚገኝ ምክክር ላይ በዘርፉ የተፈጠሩ ክፍተቶችን ለመሙላት 14 የምዘና መስፈርቶች ተዘጋጅተዋል ብለዋል፡፡

እስካሁንም ከ200 በላይ ለሆኑ ተቋማት እና ከ500 ለሚልቁ የኮንስትራክሽን ድርጅቶች ባለቤቶች ስልጠና መሰጠቱን በምክክሩ ወቅት አንስተዋል፡፡

ለአገር በቀልና ለውጭ ግብአት አቅራቢዎች ድጋፍ እየተደገ ነው ብለዋል፡፡
በዛሬው ምክክር እስከ 40,000 ብር በሆነ ገንዘብ ወጪ ቆጣቢ በሆኑ ቴክኖሎጂዎች በቀላሉ ቤቶችን ገንብተው የሚያቀርቡ ድርጅቶች ተወካዮችም መሳተፋቸውን ተመልክተናል፡፡

ምክክሩ በነገው እለትም እንደሚቀጥል ታውቋል፡፡

 

ቁልፍ ቃላት
ምላሽ