ማስታወቂያ

programs top mid size ad

ሚያዝያ 15፣ 2013- የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ትረስት ፈንድ ወላጆቻቸውን ያጡ እና ለችግር የተጋለጡ ህፃናት የሚማሩበት እና እንክብካቤ የሚገኙበት ማዕከል ገንብቶ ስራ ማስጀመሩን ተናገረ

የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ትረስት ፈንድ ወላጆቻቸውን ያጡ እና ለችግር የተጋለጡ ህፃናት የሚማሩበት እና እንክብካቤ የሚገኙበት ማዕከል ገንብቶ ስራ ማስጀመሩን ተናገረ፡፡

በአዲስ አበባ ኮልፌ አካባቢ የተገነባው የህፃናት እንክብካቤ እና የቅድመ መደበኛ ትምህርት ማዕከል በውጭ ሃገራት በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የገንዘብ ድጋፍ የተገነባ ነው ተብሏል፡፡

ከ400 በላይ ህፃናትን ተጠቃሚ ያደርጋል የተባለው ይኸው ማዕከል ሕይወት የተቀናጀ ልማት በተሰኘ ማህበር እንደሚተዳደር የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ትረስት ፈንድ በላከልን መግለጫ ተናግሯል፡፡

ለማዕከሉ ግንባታና ለህፃናት እንክብካቤ የሚውል ከ9 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ አድርጊያሁ ያለው የኢትዮጰያ ዲያስፖራ ትረስት ፈንድ ግንባታውን አጠናቆ ስራ ማስጀመሩን ተናግሯል፡፡

የተማሪዎች ምገባ፣ የጤና እና የሥነ-ልቦናና ክትትልና እንክብካቤ ከትምህርት ባሻገር በማዕከሉ የሚሰጡ አገልግሎቶች ናቸው ተብሏል፡፡

ተጠቃሚ ይሆናሉ ከተባሉ 400 ህፃናት መካከል አብዛኞቹ የተለያየ የአካል ጉዳት እና የጤና እክል ያለባቸው መሆናቸውን በመግለጫው ተናግሯል፡፡

የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ትረስት ፈንድ በቀጣይም በከፋ ድህነት ውስጥ ያሉ ኢትዮጵያውያንን ለማገዝ ውጥን አለኝ ብሏል፡፡

ለዚህም በተለያዩ የውጭ ሃገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን እና የአጋር ድርጅቶችን እገዛ እንደሚፈልግ ተናግሯል፡፡

ቁልፍ ቃላት
ምላሽ