ማስታወቂያ

programs top mid size ad

ግንቦት 6፣ 2013- በአዲስ አበባ ከደረቅ ቆሻሻ ሽያጭ 432 ሚሊየን ብር መገኘቱ ተነገረ

በአዲስ አበባ ከደረቅ ቆሻሻ  ሽያጭ 432 ሚሊየን ብር መገኘቱ ተነገረ፡፡

በዚሁ ጊዜ እንደተባለው ባለፉት 9ወራት በደረቅ ቆሻሻ መልሶ መጠቀምና ኡደት ለ3,088 ያህል ወጣቶችና ሴቶች የስራ እድል ለመፍጠር ተችሏል፡፡ 

ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደረቅ ቆሻሻ አስተዳደር ኤጀንሲ  እንደሰማነው 36,280 ቶን የኮምፓስት፣ ወረቀትና ካርቶን  እንዲሁም ፕላስቲክ ጠርሙስ ምርት መሰብሰብ ተችሏል፡፡ 

የተገኘውን የደረቅ ቆሻሻ ምርት ለአገር ውስጥና ለውጭ ገበያ  በማቅረብ ከ432 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መገኘቱን የአዲስ  አበባ ፕሬስ ስክሬታሪያትመረጃ ያሳያል፡፡

ይህንኑ የደረቅ ቆሻሻ መልሶ መጠቀምና ኡደት ስራን የሚያሳይ ኤግዚቢሽን በሚኒልክ አደባባይ በዛሬው እለት ለእይታ ክፍት መደረጉን ሰምተናል፡፡

ቁልፍ ቃላት
ምላሽ