top of page

ግንቦት 10፣2016 - ''የነበረው የአየር ሁኔታ ከሰጠሁት ትንበያ ጋር የተጣጣመ ነው'' የሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት

የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት በ2016 በልግ ወራት የነበረው የአየር ሁኔታ ከሰጠሁት ትንበያ ጋር የተጣጣመ ነው አለ።


በልጉ በኤልኒኖ ተፅዕኖ ስር እንደሚቆይና ይህም ለዝናብ መፈጠር አመቺ ሁኔታን እንደሚፈጥር ትንበያ ሰጥቶ እንደነበር ኢንስቲትዩቱ አስታውሷል።

በልግ ዋነኛ የዝናብ ወቅታቸው የሆኑት የደቡብ እና ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ አካባቢዎች ይህንኑ ያገኛሉ ማለቱንም ጠቅሷል።


ሁለቱም ከትንበያው ጋር የተጣጣሙ ሆነው መገኘታቸውን የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ፈጠነ ተሾመ ተናግረዋል ።


ኢንስቲትዩቱ በበልግ ወቅት የአየር ጠባይ ግምገማና በመጪው ክረምት ትንበያ ዙሪያ በአዳማ ከሚመለከታቸው ጋር እየመከረ ነው።


ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ቀናት በሚካሄደው በዚህ ምክክር ላይ ይመለከታቸዋል የተባሉ የፌዴራል እና የክልል ተቋማት ተወካዮች ተገኝተዋል ።


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw


Youtube: http://tiny.cc/ShegerFM1021Radio


Website: https://www.shegerfm.com/


Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page