top of page

ህዳር 10፣2017 - በ615 ወረዳዎች አጀንዳ መሰበሰቡን የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ተናገረ

እስካሁን ከ615 ወረዳዎች አጀንዳ መሰበሰቡን የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ተናገረ፡፡


ኮሚሽኑ ይህን የተናገረው ዛሬ ለህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የስራ ክንውን ሪፖርቱን ባቀረበበት ወቅት ነው፡፡


በተያዘው ወር በኦሮሚያ ክልል ካሉ ከ360 ወረዳዎች አጀንዳዎችን ተሰብስቦ እንደሚጠናቅቅ የኮሚሽኑን የክንውን ሪፖርት ያቀረቡት ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርአያ(ፕ/ር) ተናግረዋል፡፡

ኮሚሽነሩ ‘’በትጥቅ ግጭት ውስጥ ባለው የአማራ ክልልም መቶ በመቶ የተባባሪ ልየታ አድርገናል’’ ያሉ ሲሆን በክልሉ ባሉ 267 ወረዳዎቸው አጀንዳ መሰብስብ እንደሚጀመር አስረድተዋል፡፡


ኮሚሽኑ በትግራይ ክልልም በቅርቡ ስራ እንደሚጀመር ጠቁሟል፡፡


ኮሚሽነር መስፍን አርአያ በሀገሪቱ ከ1,400 በላይ ወረዳዎች መኖራቸውን ተናግረው እስካሁን ከ612 ወረዳዎች አጀንዳ ተሰብስቧል ሲሉ አስረድተዋል፡፡


ያሬድ እንዳሻው



Comentarios


bottom of page