top of page

ህዳር 10፣2017 - የልደታ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ የአቶ ሰዒድ ዓሊ ከማል ያለመከሰስ መብት ተነሳ

የአዲስ አበባ ምክር ቤት የልደታ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆኑትን፤ የአቶ ሰዒድ ዓሊ ከማል ያለመከሰስ መብትን አነሳ፡፡


ያለመከሰስ መብታቸው የተነሳው የምክር ቤቱ አባል በሙስና መጠርጠራቸው ተነግሯል፡፡


የአዲስ አበባ ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 4ተኛ ዓመት የሥራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ነው፡፡


የምክር ቤቱ አባልና የልደታ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆኑትን የአቶ ሰዒድ ዓሊ ከማል ያለመከሰስ መብትን የተነሣው በፍትሕ ሚኒስቴር በቀረበ ጥያቄ መሠረት መሆኑን በምክር ቤቱ የሰላም፣ የፍትሕ እና መልካም አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ ተናግሯል።

ቋሚ ኮሚቴው በሚኒስቴሩ የቀረበውን የሙስና ክስ በመመርመር የደረሰበትን ውጤት ለምክር ቤቱ ዝርዝር ሪፖርት አቅርቧል።


ምክር ቤቱ የቀረበው ሪፖርትን በመመልከት፤ በተጠረጠሩበት የሙስና ወንጀል በሕግ እንዲጠየቁ ለማድረግ ያለመከሰስ መብታቸው እንዲነሳ በሙሉ ድምፅ ወስኗል፡፡


ያሬድ እንዳሻው



Comments


bottom of page