የዩኒቨርሲቲ መምህራንን ለመፈተን እየተዘጋጀሁ ነው ሲል ትምህርት ሚኒስቴር ተናገረ፡፡
ትምህርት ሚኒስቴር ባሻሻለው ስርዓተ ትምህርት መሠረት የመውጫ ፈተና በሚል ለቅድመ ምረቃ ተማሪዎች ሀገር አቀፍ ፈተና መስጠት መጀመሩ ይታወቃል።
በዚህ መመዘኛም የማለፊያ ውጤት ሳያመጡ የሚቀሩ #ተመራቂ_ተማሪዎች ቁጥርም ጥቂት የሚባል አይደለም።
ይህንን ተከትሎም ብዙዎች መጀመሪያ መመዘን ያለበት መምህሩ ነው፤ ተፈትኖ ብቃቱ በታወቀ #መምህር የተማረን ተማሪ ነው መፈተን የሚገባው ሲሉ ይደመጣሉ።
ሸገር ራዲዮ ይህንን ጥያቄ ለትምህርት ሚኒስቴር አቅርቦ፤ በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚያስተምሩ መምህራንን ብቃት ለመመዘንም ፈተና ሊፈትናቸዉ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ሰምቷል።
ይህንን የነገሩን በሚኒስቴሩ የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አገልግሎት ዳይሬክተር የሆኑት እዮብ አየነው(ዶ/ር ) ናቸው።
‘’የመምህራን ፈተና ከዚህ በፊት በአንደኛ ደረጃ በሚያስተምሩት ላይ ተሞክሮ ነበረ በመሆኑም አልተጀመረም ማለት አይቻልም’’ ያሉት ዳይሬክተሩ አሁን ግን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራንን ለመፈተን ዝግጅት እየተደረገ እንደሆነ አስረድተዋል።
ዝግጅቱ እንዳለቀ በዚህ ዓመት ወይም በቀጣዩ 2018 ዓመት ለ #ከፍተኛ_የትምህርት_ተቋማት_መመህራን ፈተና መሰጠት ይጀምራል ብለዋል።
እስካሁን ባለው ስርአት የዩኒቨርስቲ መምህራን ማስተማር ከመጀመራቸው በፊት ያለው አንድ ዓመት፤ እንዴት ማስተማር እንዳለባቸው በተለያዩ ዘዴዎች ትምህርት እንዲያገኙ ይደረጋሉ ሲሉ ተናግረዋል።
ነገር ግን ይህ በቂ ስላልሆነ ማሻሻያ የሚያስፈልገው ነው ብለዋል።
ማንያዘዋል ጌታሁን
Comments