ሰላምን ማረጋገጥ ካልተቻለ የአፍሪካን የልማት ግብ ለማሳካት እንደማይቻል ተነገረ፡፡
ይህ የተነገረው ዛሬ በአዲስ አበባ ስካይ ላይት ሆቴል አህጉር አቀፍ የሰላም፣ የብልፅግናና የልማት ኮንፍረንስ እየተካሄደ ባለበት መድረክ ላይ ነው፡፡
በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢትዮጶያ የሰብአዊ መብት አስተባባሪ የሆኑት ራሚዝ አላክባሮቭ(ዶ/ር) አለም መስቀለኛ መንገድ ላይ መሆኗን ተናግረው ሰላምን ማረጋገጥ እና ማስፈን ካልተቻለ የአፍሪካን የልማት ግብ በአፍሪካ ለማሳካት እንደማይቻል ተናግረዋል፡፡
ሰላም እና ደህንነት ዘላቂ የልማት ግብን ለማረጋገጥ መሰረቶች ናቸው ብለዋል፡፡
ሌላው በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት በአፍሪካ ህብረት የፖለቲካ ጉዳዮች የሰላም እና የደህንነት ኮሚሽነር አምባሳደር ባንኮሌ አዲኦየ በኢትዮጵያ በአፍሪካ ሰላምን ለማስፈን የአፍሪካ ህብረት የተቻለውን እያደረገ እንዳለ ተናግረው ለተአድሶ ኮሚሽን የቀድሞ ተዋጊዎችን መልሶ ለማቋቋም 1 ሚሊዮን ዶላር ለግሷል፡፡
ይህም ሰላም ላይ መስራት አስፈላጊ መሆኑን ስላመነ ነው ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ ላይ ለሰላም ኢንቨስት ማድረግ የአፍሪካ ቀንድ ላይ እና በመላው አህጉራችን ኢንቨስት እንደማድረግ እንቆጥረዋለን ብለዋል፡፡
ለኢትዮጵያ ፕሬዘዳንት ታዬ አፅቀስላሴ በበኩላቸው ኢትዮጵያ ሰሞኑን የጀመረችው የቀድሞ ተዋጊዎችን መልሶ ወደ ማህበረሰቡ የማቀላቀል ስራ ሰላምን ለማስፈን ያላትን ቁርጠኝነት ያሳያል ብለዋል፡፡
በአፍሪካ ቀጣይነት ያለው ሰላም ለማስፈን ሴቶችና ወጣቶች ላይ መስራትም ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
ያሬድ እንዳሻው
Comments