top of page

ህዳር 17፣2017 - የጤና ተቋማት የመድሃኒትና የህክምና መሳሪያ እጥረት ችግር ለመፍታት ምን እየተሰራ ነው?

የፌዴራል መንግስት የዘንድሮ አጠቃላይ በጀት 1.5 ትሪሊዮን መደረሱ ህዝቡን ለተጨማሪ ግብር የሚዳርግ እና የሚያማርር ሊሆን ይችላል ሲሉ የፓርላማ አባላት ተናገሩ፡፡


የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ይህን ያሉት የፌዴራል መንግስት የ2017 በጀት ዓመት ተጨማሪ በጀትን ለማጽደቅ በቀረበ ረቂቅ አዋጅ ላይ ባደረጉት ወይይት ነው፡፡


የ2017 በጀት ዓመት የፌደራል መንግስት መደበኛ በጀት ከዚህ ቀደም 971.2 ቢሊዮን ሆኖ መጽደቁ ይታወቃል፡፡


ይሁንና ከ2017 አስከ 2021 ድረስ የተነደፈውን የማክሮ ኢኮኖሚ እና የፊስካል ፖሊሲ ማዕቀፍ ማሻሽያ ተከትሎ ከታክስና ከወጪ ፋይናንስ የሚገኘውን ገቢ በመጨመሩ ለመደበኛ ስራዎች እና የወጪ አሽፋፋን ለማስተካከል ተጨማሪ በጀት ማጽደቅ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል ተብሏል፡፡

ተጨማሪ በጀቱ ለዕዳ ክፍያ፣ ለማህበራዊ ድጋፍ፣ ለካፒታል ፕሮጀክቶች ማስተካከያ እንዲሆን መታሰቡን በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መንግስት ተጠሪ ሚኒስትሩ ተስፋዬ ቤልጂጌ ተናግረዋል፡፡


በዚህም ለበጀት ዓመቱ ያስፈለገው ተጨማሪ በጀት 582 ቢሊዮን ብር ነው ብለዋል፡፡


ለመደበኛ ወጪ 393 ቢሊዮን ብር፣ ለካፒታል ወጪ 70 ቢሊዮን እና ለወጪ አሸፋፈን 119 ቢሊዮን ብር ሆኖ ቀርበዋል፡፡


የምክር ቤት አባላት በበኩላቸው ተጨማሪ በጀቱ የተጋነነ ነው የሚል ጥያቄ አንስተዋል፡፡


ህዝቡንም ለተጨማሪ የግብር የሚዳርግ እና የሚያማርር ሊሆን ይችላል ሲሉ የፓርላማ አባላት ሃሳባቸውን እያቀረቡ ነው፡፡


ምክር ቤቱ የ2017 በጀት ዓመት የፌዴራል መንግሥት ተጨማሪ 582 ቢሊየን ብር በጀትን አጽድቋል፡፡


ያሬድ እንዳሻው

Comments


bottom of page