top of page

ህዳር 19፣2017 - ''ግጭት ባለባቸው አካባቢዎች አምቡላንሶች እየወደሙ በጤናው ዘርፍ መስተጓጉሎች እየተፈጠሩ ነው'' የጤና ሚኒስቴር

ግጭት ባለባቸው አካባቢዎች አምቡላንሶች እየወደሙ በመሆኑ በጤናው ዘርፍ መስተጓጉሎች እየተፈጠሩ ነው ሲል የጤና ሚኒስቴር ተናገረ፡፡


በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ከፍተኛ የአምቡላንስ እጥረት እንዳለ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ተናግረዋል፡፡


በዚህም የተነሳ እናቶች በወሊድ ወቅት እየተቸገሩ እንዲሁም ሌሎች ታማሚዎችም ከአንድ የጤና ተቋም ወደ ሌላው ለማዘዋወር ከፍተኛ ችግር እያጋጠመ ነው ተብሏል፡፡


እንደራሴዎች ይህንን ችግር ለመፍታት የጤና ሚኒስቴር ምን እየሰራ እንደሆነ ጠይቀዋል፡፡

የጤና ሚኒስትር መቅደስ ዳባ(ዶ/ር) በሀገሪቱ የአምቡላንስ እጥረት ከመኖሩም ባሻገር በተለይም ግጭት ባለባቸው ቦታዎች የሚገኙ አምቡላንሶች መውደማቸው ተጨማሪ ችግር እንደሆነ ጠቅሰዋል፡፡


እንደ ሀገር የገጠመውን የአምቡላንስ እጥረት ችግር ለመቀነስ መስሪያ ቤታቸው የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ እንደሆ አስረድተዋል፡፡

ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ ጤና ሚኒስቴር  3,014 አምቡላንሶችን ገዝቶ በሁሉም ክልል ለሚገኙ የጤና ተቋማት አከፋፍሏል ብለዋል፡፡


በተጨማሪ እንደ አምቡላንስ ሆነው ድጋፍ የሚሰጡ ከ200 በላይ ፒክአፕ መሰል ተሽከርካሪዎችም ተሰራጭተዋል ሲሉ ተናግረዋል፡፡


የጤና ተቋማት ራቅ ለሚልባቸው ነዋሪዎች የሚሆኑም 572 ሞተር ሳይክሎች ተከፋፍለው የጤናው ዘርፍ አገልግሎት እንዲያግዙ ተደርጓል ብለዋል ሚኒስትሯ፡፡


ማንያዘዋል ጌታሁን

Comments


bottom of page