የዲጅታል አገልግሎቱን ለማስፋት "ባንክዎን በእጅዎ" በሚል ሀሳብ ለአንድ ወር የሚቆይ የዲጅታል ባንኪንግ መረሀ ግብር ማዘጋጀቱን አዋሽ ባንክ ተናገረ።
ከዛሬ እስከ ታህሳስ 30 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ይቆያል የተባለው ይሄው መረሀ ግብር የባንኩን ዋና መስሪያ ቤት ጨምሮ በሁሉም የባንኩ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶቹ ይካሄዳል ተብሏል።
በዚህም አዋሽ ብር ፕሮ ሞባይል ባንኪንግ፣ አዋሽ ብር ፕሮ መርቻንት እና የፖስ መርቻንት አገልግሎቶችን ባንኩ ለማስተዋወቅ ማቀዱን ዋና ስራ አስፈፃሚው አቶ ፀሃይ ሽፈራሁ ተናግረዋል።
ባንኩ አዋሽ ብር ፕሮ ሞባይል ባንኪንግ ብሎ ለደንበኞቹ ያቀረበው አገልግሎት በ7 የተለያዩ ቋንቋዎች መጠቀም እንዲቻል ተደርጎ የተሰራ መሆኑም ተናግሯል፡፡
ደንበኞች መተግበሪያውን ተጠቅመው የአየር ሰዓት መሙላት፣ የተለያዩ የአገልግሎቶች ክፍያዎችን ማለትም የትምህርት፣ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ክፍያ እና ሌላ ሌላም ማከናወን የሚችሉበት እንደሆነ ተነግሯል።
በተጨማሪም በተመሳሳይ መተግበሪያ ከወለድ ነፃ ባንኪንግ አገልግሎት ለኢ ኽላስ ተጠቃሚ ደንበኞቼ አቅርቤያለሁ ብሏል።
ለአንድ ወር በሚቆየው የዲጅታል ባንኪንግ ተጠቃሚ ደንበኞች በየሳምንቱ 13 የሳምሰንግ ቀንጡ የሞባይል ቀፎዎች በአጠቃላይ 52 የሞባይል ቀፎዎች በስጦታ አበረክታለው ያለው አዋሽ ባንክ የገንዘብ ሽልማትም አለኝ ብሏል።
ደንበኞችን በተለይም ዲጅታል ባንኪንግ የማይጠቀሙትን ወደ መስመሩ ማስገባት፣ ግንዛቤ መፍጠር እና ክፍያዎችን በዲጅታል ባንኪንግ እንዲከናወኑ ማድረግ ላይ በአንድ ወር ውስጥ ይሰራል መባሉን ሰምተናል።
ፋሲካ ሙሉወርቅ
Commentaires