በኢትዮጵያ በኑሮ ውድነቱ ጎዳና ወጥተው “ልጆቼን የማበላቸሁ አጣው የሚሉ አዛውንቶች እና ራበኝ የሚሉ አንጀት የሚበሉ ህጻናትን” በከተማችን ቁጥራቸው እየጨመረ መሆኑን እንደታዘቡ የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት አባላት ተናገሩ፡፡
ይህን ያሉት አቶ አበረ አዳሙ የተባሉ አንድ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ናቸው፡፡
አቶ አበረ አዳሙ የተባሉ የምክር ቤት አባሉ ይህን የተናገሩት የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር ከምክር ቤት አባላት ለሚቀርቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት በተሰየሙበት መድረክ ላይ ነው፡፡
‘’የሀገር ውስጥ ምርቶች ላይ የሚደረገው ያለ ምክንያት ጭማሪ የህዝቡን ኑሮ እንዲመሰቃቀል እያደረገው ነው ያሉት አቶ አበረ ይህን ለመፍታት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ምን እየሰራ ነው?’’ ሲሉ ጠይቀዋል፡፡
በመስሪያ ቤቱ የሚወሰዱ እርምጃዎችም ምን ውጤት አምጥተዋል? ሲሉ የምክር ቤት አባሉ ጠይቀዋል፡፡
ለጥያቄዎች ምላሽ የሰጡት የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር) ‘’የዋጋ ንረቱን ለማረጋጋት ባለፉት አስር ዓመታት ተወስዶ የማይታወቅ እርምጃ ወስደናል’’ ብለዋል፡፡
ሚኒስቴሩ ዋጋ ግሽበቱ ቋሚ ገቢ ያላቸው ሰዎች ላይ ጠንካራ ክንዱን እያሰረፈ መሆኑን አምኗል፡፡
ባለፉት አምስት ወራት ብቻ በ105,000 ነጋዴዎች ላይ እርምጃ ተወስዷል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ድሬዳዋን ጨምሮ በሁሉም ክልሎች ያሉ 283 ህገ-ወጥ ኬላዎች አሉ እነዚህ ኬላዎች የዋጋ ንረቱ ላይ ተጽዕኖ እያሳደሩ በመሆናቸው ፓርላማው መፍትሄ እንዲሰጥ ሚኒስትሩ ጠይቀዋል፡፡
ለሚኒስትሩ ሌሎችም ጥያቄዎች ቀርበውላቸው ምላሽ ሲሰጡ አርፍደዋል፡፡
ያሬድ እንዳሻው
Commentaires