የቀድሞ ተዋጊዎች መልሶ ለማቋቋም በትግራይ የተጀመረውን ስራ በእቅዱ መሰረት ለመጨረስ የብሔራዊ የተሃድሶ ኮሚሽን የቅበላ አቅሙን ጨምሯል ተባለ፡፡
ለ #ፕሪቶሪያው አንቀፅ 8 ስምምነትን መሰረት በማድረግ የብሔራዊ ተሀድሶ ኮሚሽን ከሁለት ሳምንት በፊት የቀድሞ የትግራይ ተዋጊዎችን በመቀበሌ በሁለት ካምፖች በማስገባት የተሃድሶ ስልጠና መጀመሩና እስካሁንም የተወሰኑ የቀድሞ ተዋጊዎች ስልጠና ጨርሰው ወደየ አካባቢያቸው መሄዳቸውን ሰምተናል፡፡
የብሔራዊ የተሃድሶ ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ተመስገን ጥላሁን ለሸገር እንደተናገሩት በመጪዎቹ አራት ወራት የመጀመሪያው ዙር #የቀድሞ_ተዋጊዎችን በማሰልጠንና የመቋቋሚያ ገንዘብ በመስጠት ሰላማዊ ሕይወትን እንዲኖሩ ለማድረግ የተጀመረው ስራ በመልካም ሁኔታ እየሄዱ መሆኑንና እቅዳቸውን ለማሳካት የቅበላ ቁጥሩን ከፍ ማድረግ አስፈልጓል ሲሉ ዋና ኮሚሽነሩ ለሸገር ሬዲዮ ነግረዋል፡፡
ኮሚሽኑ አስቀድሞ በያዘው እቅድ መሰረት በየእለቱ 320 የቀድሞ ተዋጊዎችን ለመቀበል ዝግጅት አድርጎ የነበረ ሲሆን አሁን ግን የየእለት ቁጥሩን በእጥፍ ከፍ ማድረጉን ተናግሯል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…
የኔነህ ሲሳይ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Website: https://shorturl.at/yCz7q
📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comentários