top of page

ህዳር 25፣2017 - በአዲስ አበባ ከዚህ ቀደም በዲጂታል መላ ያልተመዘገቡ የነዋሪነት መታወቂያ፣ ያገባ፣ ያላገባ አገልግሎቶችን የሲስተም ችግር በማጋጠሙ በአብዛኛው መሰጠት ማቆማቸው ተሰማ

በአዲስ አበባ ከዚህ ቀደም በዲጂታል መላ ያልተመዘገቡ የነዋሪነት መታወቂያ፣ ያገባ፣ ያላገባ አገልግሎቶችን የሲስተም ችግር በማጋጠሙ በአብዛኛው መሰጠት ማቆማቸው ተሰማ፡፡


አገልግሎቶቹ የቆሙት፤ ተመዝጋቢዎች መዝግቦ አሻራ የሚወስደው ማሽን እክል ስላጋጠመው ነው ተብሏል፡፡


ሆኖም ሙሉ በሙሉ ቆሟል ማለት እንዳልሆነ እና ከዚህ ቀደም በዲጂታል የተመዘገብ የከተማዋ ነዋሪዋች ኤጀንሲው የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ማግኘት እንደሚችሉ ሰምተናል፡፡



የተፈጠረው የሲስተም የመቆራረጥ ችግር ሳምንታትን ያስቆጠረ ሲሆን መንስኤውን እና መፍትሄውን ለመፈለግ ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በመሆን እየሰራን ነው ሲሉ የአዲስ አበባ የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ዋና ዳሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ ነግረውናል፡፡


ዋና ዳሬክተሩ አክለውም ‘’የተቋረጠውን አገልግሎት ስንጀምር ለህብረተሰቡ እናሳውቃለን’’ ያሉ ሲሆን ‘’ለተፈጠረው መጉላላት ይቅርታ እንጠይቃለን’’ም ብሏል፡


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…

ማርታ በቀለ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g


📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s


Comments


bottom of page