top of page

ህዳር 25፣2017 - በኢትዮጵያ በካፒታል ገበያ የሙዓለ ነዋይ ኢንቨስትመንት አማካሪ የመጀመሪያው የሀገር ቤት የግል ድርጅትፈቃድ ማግኘቱ ተሰማ

በኢትዮጵያ በካፒታል ገበያ የሙዓለ ነዋይ ኢንቨስትመንት አማካሪ የመጀመሪያው የሀገር ቤት የግል ድርጅት ‘’አይ ካፒታል ኢንስቲትዩት’’ ፈቃድ ማግኘቱ ተሰማ፡፡


አይ ካፒታል ኢንስቲትዩት በየዓመቱ በፋይናንስና አካባቢው ሰፊ የፋይናንስ ጉባኤ ከማዘጋጀት ባለፈ በካፒታል ገበያው የሙዓለ ነዋይ ኢንቨስትመንት አማካሪ መሆኑ ምን እድል እንደሚያመጣላቸው ጠይቀናቸዋል።

የአይ ካፒታል ኢንስቲትዩት ዋና ስራ አስፈፃሚ ገመቹ ዋቅቶላ (ዶ/ር) በሀገር ቤት የመጀመርያው ሀገር በቀል አማካሪ ለመሆን በኢትዮዽያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ሰፊ መስፈርትና ደረጃዎች እንደተጠየቁ ነግረውናል።


በካፒታል ገበያ የሙአለ ነዋይ ኢንቨስትመንት የማማከር ተግባር አከናውን ተብሎ ፈቃድ የጨበጠው ኢንስቲትዩቲ ከፊቱ ሰፊ ስራ እንደሚጠብቀውና ለኢንቨስተሩም የተሻለ ምክር ለመስጠት በቦርድና በአለምአቀፍ ደረጃ መዋቀሩን ነግሮናል።


በኢትዮዽያ በተለያየ የቢዝነስና የካፒታል ገበያ ለመሳተፍ ለግለሰብም ለፋይናንስ ተቋምም ሆነ ለድርጅቶች የኢንቨስትመንት ምክር ለመስጠት ፈቃድ ያገኙት ድርጅቶች ሶስት ናቸው።


ከነዚህ ውስጥ ሁለቱ የውጭ ሲሆኑ አንደኛው ሀገር በቀል መሆኑ ታውቋል።


ተህቦ ንጉሴ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g


📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s


Comments


bottom of page