ህዳር 27፣ 2015- የሱዳን ወታደራዊ መንግስት መሪዎች እና ተቃዋሚዎቻቸው አገሪቱን ወደ ህዝባዊ አስተዳደር ለመመለስ በሚደረገው ሽግግር ላይ ተስማሙ፡፡
- sheger1021fm
- Dec 6, 2022
- 1 min read
ህዳር 27፣ 2015
የሱዳን ወታደራዊ መንግስት መሪዎች እና ተቃዋሚዎቻቸው አገሪቱን ወደ ህዝባዊ አስተዳደር ለመመለስ በሚደረገው ሽግግር ላይ ተስማሙ፡፡
ሽግግሩ በአገሪቱ ምርጫ እስኪካሄድ ለ2 ዓመታት እንደሚዘልቅ አፍሪካ ኒውስ ፅፏል፡፡
ከጦር አለቆቹ ጋር ስምምነቱን ከተፈራረሙት መካከል የነፃነት እና የለውጥ ሀይሎች የተሰኘው ጥምረት አንዱ መሆኑ ታውቋል፡፡
ስምምነቱን ያልፈረሙ የተቃውሞ ሀይሎች እንዳሉ በዘገባው ተጠቅሷል፡፡
የስምምነቱ ተቃራኒዎች የተቃውሞ ሰልፍ መጥራታቸው ተሰምቷል፡፡
የሱዳን የጦር አለቆች ከአመት በፊት ዳግም ግልበጣ ከፈፀሙ በኋላ አገሪቱ በፖለቲካዊ ቀውስ ስትናጥ መቆየቷን ዘገባው አስታውሷል፡፡
የኔነህ ከበደ

ሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
https://bit.ly/33KMCqz
Comments