ህዳር 28፣ 2015
ሩዋንዳ በምስራቃዊ ኮንጎ ኪንሻሣው M-23 አማፂ ቡድን የተነሳ ከአሜሪካ ጋር ክፉ ደግ እየተነጋገረች ነው ተባለ፡፡
ኮንጎ ኪንሻሣ ጎረቤት ሩዋንዳ የአማፂው ቡድን አይዞህ ባይ ነች ስትል መቆየቷን አፍሪካ ኒውስ አስታውሷል፡፡
የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን የኮንጎ ኪንሻሣን ክስ በማስተጋባት ሩዋንዳን M-23 ን መርዳትሽን አቁሚ ማለታቸው ተሰምቷል፡፡
ይሄን ተከትሎ የሩዋንዳ መንግስት የምስራቃዊ ኮንጎ ኪንሻሣውን የፀጥታ መደፍረስ በማባባስ ላይ ያለው አለም አቀፉ ማህበረሰብ ነው ማለቱ በዘገባው ተጠቅሷል፡፡
ሩዋንዳ በምስራቃዊው የኮንጎ ኪንሻሣ ግጭት እጄ የለበትም ስትል እንደምትምል እና እንደምትገዛት ዘገባው አስታውሷል፡፡
የኔነህ ከበደ
ሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Comments