ህዳር 28፣ 2015
ዘንድሮ በተወሰነ ወራት ውስጥ የማዕድን ሚኒስቴር ከ220 ቶን በላይ ቁርጥራጭ ብረቶችን ሰብስቤያሁ አለ፡፡
የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ብረቶቹን የሰበሰው ከተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤቶች እንደሆነ ለሸገር ተናግሯል፡፡
መንግስት ለብረት ምርት ከዚህ በኋላ የውጭ ምንዛሪ አልሰጥም ማለቱን ተከትሎ የማዕድን ሚኒስቴር የተከማቹ ቁርጥራጭ ብረቶች ለሐገር ቤት ብረት አምራቾች እንዲወስዱ እያገዘ ነው፡፡
ከግብርና ሚኒስቴር 2.540 ቶን ቁርጥራጭ ብረት ተሰብስቧል፡፡
ከማዕድን ሚኒስቴር 116.28 ቶን ተነስቶ ቀሪው እየተነሳ መሆኑን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለሸገር ነግሯል፡፡
ከቤተ መንግስትና ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 47 ቶን ፤ ከመስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር 7.1 ቶን ብረት ተሰብስቧል።
ከውሃ ስራዎች 3.26 ቶን ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ 2.38 ቶን ቁርጥራጭ ብረት ተነስቷል ተብሏል፡፡
ከድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ 24 ቶን፣ ከኢትዮጵያ ምግብና መድሃኒት ባለስልጣን 3.8 ቶን የተጣለ ብረት እና ከፍትህ ሚኒስቴር አንድ ቶን አልሙኒየም መሰብሰቡን ሰምተናል፡፡
ማዕድን ሚኒስቴር በኢትዮጵያ በየመንግስት መስሪያ ቤትና ቦታዎች የተጣሉት ቁርጥራጭ ብረቶች ለ2 ዓመት ያህል ለሐገር ቤት ብረት አምራቾችን ፍጆታ የውጭ ምንዛሪ ፈፅሞ ሳይጠይቁ እንደሚበቃቸው በጥናት አረጋግጫለሁ ብሏል፡፡
የተለቀሙት ቁርጥራጭ ብረቶች ሐገር ቤት ላሉ ከ20 ለሚበልጡ ብረት አምራቾች ተከፋፍሎ እንዲወስዱ ተደልድሎላቸዋል፡፡
ከነዚህ ውስጥ RMI ብረት አምራች 1 ሺ 417.9 ቁርጥራጭ ብረት፡፡
የሱ የተባለ ብረት አምራች 400 ቶን፣ ኢስት 72 ቶን፣ አቢሲኒያ 20 ቶን ቁርጥራጭ ብረት እንዲወስዱ ተደልድሎላቸዋል፡፡
20 ግድም የሚደርሱት ቀሪዎቹ የብረት ፋብሪካዎች የተመደበላቸው የቁርጥራጭ ብረት እንዲወስዱ መጠኑ ተደልድሎላቸዋል ተብሏል፡፡
በኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ከተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ከቤተ መንግስት ከገንዘብና ከተለያዩ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ቁርጥራጭ ብረቱ ወደፊትም እንደሚሰበሰብ የማዕድን ሚኒስቴር የለያቸው ቦታዎች መሆኑን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለሸገር ነግሯል፡፡
ተህቦ ንጉሴ
ሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Comments