ህዳር 29፣ 2015
የቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂን
ፒንግ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ሳውዲ አረቢያ መግባታቸው ተሰማ፡፡
ሺ ጂን ፒንግ በሳውዲ ጉብኝታቸው ፈርጀ ብዙ ጉዳዮች እንደሚጠብቋቸው ሚድል ኢስት ሞኒተር ፅፏል፡፡
የቻይናው መሪ ከሳውዲ አረቢያ ሹሞች ጋር በበርካታ ጉዳዮች ከሚያደርጉት ንግግር በተጨማሪ ከባሕረ ሰላጤው በአጠቃላይም ከአረብ አገሮች መሪዎች ጋር እንደሚነጋገሩ ታውቋል፡፡
የሺ ጂን ፒንግ የሳውዲ አረቢያ ተልዕኮ በቻይና እና በአረብ አገሮች መካከል ያለውን ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ እንደሚያሸጋግረው ተገምቷል፡፡
ከሁለቱም ወገኖች በኩል ተመሳሳይ ፍላጎት እንዳለ ዘገባው አስታውሷል፡፡
የኔነህ ከበደ
ሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
https://bit.ly/33KMCqz
Comments