top of page

ህዳር 3፣ 2017 - ‘’በትጥቅ አመጽ ይንቀሳቀሱ ከነበሩት ጋር ስምምነት ፈጥሬ በጋራ እየሰራን ነው’’ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል

‘’በትጥቅ አመጽ ይንቀሳቀሱ ከነበሩት ጋር ስምምነት ፈጥሬ በጋራ እየሰራን ነው’’ ሲል የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ተናገረ፡፡


ወደ ሰላም የተመለሱ ታጣቂዎችን በካቢኒ አባልነትን ጨምሮ በተለያዩ የስራ መስኮች በመሳተፍ እየሰሩ ይገኛሉ ተብሏል፡፡


በክልሉ በአሁን ሰዓት ምንም አይነት የሚያሰጋ የጸጥታ ችግር የለም ሲል ክልሉ ለሸገር ራዲዮ ነግሯል፡፡


መንግስትን በመቃወም ጫካ ገብተው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የተለያዩ ቡድኖች ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ትጥቅ ፈትተዋል ተብሏል፡፡

ይህንን ለሸገር የነገሩት፤ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በሰላም ግንባታና ጸጥታ ቢሮ የሰላም ግንባታ ዘርፍ ምክትል ቢሮ ሀላፊ ጸሀይ ጉዮ ናቸው፡፡


በክልሉ ቀድሞ የነበረው የጸጥታ ችግር ጥሎት ያለፈው ክፍተቶችን ለማስተካከል እየተሰራ እንደሆነም አስረድተዋል፡፡


ይሁንና ወደ ሰላም የተመሱት ለመደገፍ ክልሉ የፋይናንስ እጥረት እንደገጠመው አቶ ጸሀይ ጠቅሰዋል፡፡


''ይህንን ክፍተት ለማስተካከልም እየተሰራ ነው'' ብለዋል፡፡


ማንያዘዋል ጌታሁን

Comments


bottom of page