የተሳከረውን የሪል ስቴት ገበያ መፍትሄ ያቀርባል የተባለው በኦዲተሮችና በሂሳብ ባለሙያዎች ሀሳብ ያዋጣል የተባለ እንዲሁም በአጠቃላይ በካፒታል ገበያ እና ኢንቨስትመንት እድል ዙሪያ የተሻለውን ያመጣል የሚል ሰፊ አለም አቀፍ ጉባኤ አዲስ አበባ ልታስተናግድ ነው፡፡
ይህ አለም አቀፍ ጉባኤ ከሀገር ውስጥ የብሔራዊ ባንክን፣ የገንዘብ ሚኒስቴርን እንዲሁም ከውጪ የአለም ባንክን የአፍሪካ ልማት ባንክና ዩኤንዲፒ(UNDP)ን እንደሚያሳትፍ ከአዘጋጆቹ ሰምተናል፡፡
በዚህ ጉባኤ የካፒታል ገበያው ቁጥጥር እንዲበረታ ዘላቂ የፋይናንስ ስርአት እንዲኖር ይመከርበታል ተብሏል።
አለም አቀፍ ልምድና ተሞክሮው ምንድነው? ፊንቴክና የቴክኖሎጂ ፈጠራ ከገበያው ጋር እንዴት ይጣጣማል በሚለው ጉዳይ ሀሳብ ይዋጣበታል ተብሏል።
ይህ አለም አቀፍ ጉባኤ ለሶስት ቀን እንደሚቆይ ከአዘጋጆቹ ሰምተናል።
በኢትዮዽያ ካፒታል ገበያ ከፍተኛ አማካሪ የሆኑት አቶ ዮሐንስ አረጋ፤ ከዚህ ጉባኤ የሚነሱት ሀሳቦችና ልምዶች ለገበያው ጥንካሬና ቁጥጥር የሚያዋጣው እንዳለ ለሸገር 102.1 ራዲዮ ነግረዋል።
ተህቦ ንጉሴ
Comments