ህዳር 30፣ 2015
መቀመጫውን በትሪፖሊ ያደረገው የሊቢያ መንግስት ግሪክ ሉዓላዊነታችንን እየተዳፈረች ነው ሲል ቁጣውን አሰማ፡፡
የትሪፖሊው መንግስት ባወጣው መግለጫ ግሪክ የባሕር ወሰናችንን እየተጋፋች ነው ማለቱን ዴይሊ ሳባሕ ፅፏል፡፡
እንደሚባለው ግሪክ ከክሬት ደሴት በስተደቡብ እና ደቡብ ምዕራብ የነዳጅ እና የተፈጥሮ ጋዝ ፍለጋ እያካሄደች ነው፡፡
ሊቢያ ደግሞ ይሄ በምስራቃዊ ሜዴትሬኒያን የሚገኝ የባህር ክፍል የገዛ የውሃ አካሌ ነው ትላለች፡፡
ግሪክ በበኩሏ ከ3 ዓመታት በፊት በቱርክ እና በሊቢያ መካከል የተደረሰውንየባህር ወሰን መከለያ ስምምነት እንደተቃወመችው ዘገባው አስታውሷል፡፡
የኔነህ ከበደ
ሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Comentarios