ህዳር 30፣ 2015
ቡና ባንክ ጠቅላላ ሀብቴ ወደ 34.1 ቢሊየን ብር አድጓል አለ፡፡
ባንኩ በዘንድሮ የስራ ዘመን 1.25 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘቱን ተናግሯል፡፡
ቡና ባንክ ተቀማጭ የገንዘብ መጠኑ በ6.7 ቢሊየን አድጎ 27.2 ቢሊየን ብር መድረሱን ሰምተናል፡፡
በበጀት ዓመቱ 7.6 ቢሊየን ብር ብድር ሰጥቻለሁ ብሏል፡፡
ባንኩ በጠቅላላ 25.85 ቢሊየን ብር ብድር መስጠቱን ከሪፖርቱ አንብበናል።
በዘንድሮ አፈፃፀም 149.1 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ሰብስቧል ይህ ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር ዝቅተኛ መሆኑን ሰምተናል፡፡
የመክፈያ ጊዜ ያለፈባቸው ብድሮች ከጠቅላላ ብድር ያላቸው ምጣኔ 4.1 ነው።
ይህም ብሔራዊ ባንክ ካስቀመጠው የ5 በመቶ ጣሪያ ያነሰ ሆኖ መመዝገቡን ቡና ባንክ ተናግሯል፡፡
ተህቦ ንጉሴ
ሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
https://bit.ly/33KMCqz
ความคิดเห็น