top of page

ህዳር 30፣ 2015የደቡብ አፍሪካው የቀድሞ የጤና ሚኒስትር ዝዌሊ ምኬዜ ለገዢው የአፍሪካ ብሔራዊ ኮንግረስ (ANC) መሪነት በሚደረገው ፉክክር የፕሬዚዳንት

  • sheger1021fm
  • Dec 9, 2022
  • 1 min read

ህዳር 30፣ 2015


የደቡብ አፍሪካው የቀድሞ የጤና ሚኒስትር ዝዌሊ ምኬዜ ለገዢው የአፍሪካ ብሔራዊ ኮንግረስ (ANC) መሪነት በሚደረገው ፉክክር የፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሣ ዋነኛ ተፎካካሪ ይሆናሉ ተባለ፡፡


ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሣ ከፋላ ፋላ እርስታቸው በጥሬ ገንዘብ 4 ሚሊዮን ዶላር መዘረፉን ለመሸፋፈን ሞክረዋል ተብለው ፖለቲካዊ መካለብ እንዳጋጠማቸው አፍሪካ ኒውስ ፅፏል፡፡


ከ ANC አንዳንድ ወገኖችም ሳይቀር ስልጣን እንዲለቁ ግፊት እየተደረገባቸው ነው፡፡


የአገሪቱ ፓርላማም በመጪው ሳምንት በራማፎሣ ጉዳይ እንደሚነጋገር ታውቋል፡፡


የገዢው የአፍሪካ ብሔራዊ ኮንግረስ (ANC) መሪ ሆኖ የሚመረጥ ግለሰብ የአገሪቱ ፕሬዚዳንት የመሆን እድሉ የሰፋ ነው፡፡



በዚህም የተነሳ የፖለቲካ ማህበሩ የመሪዎች ምርጫ ከፍተኛ ትኩረት እያገኘ ነው ተብሏል፡፡


የኔነህ ከበደ


ሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page