ህዳር 4፣2017-መንግስት ለሽያጭ ለሚያቀርባቸው 900 ቢሊየን ብር የሚያወጣ የግምጃቤት ሰነድ ገንዘቡን ከየት አምጥቶ ይከፍላል?
- sheger1021fm
- Nov 14, 2024
- 1 min read
ለመንግስት የልማት ድርጅቶች በሰጠውና ባልተመለሰለት ወደ 900 ቢሊዮን ብር የተጠጋ ብድር ምክንያት ሊፈርስ ነበር የተባለውን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ለማትረፍ መንግስት እዳውን የሚመጥን የግምጃ ቤት ሰነድ ለሽያጭ ሊያቀርብ መሆኑ ታውቋል፡፡
የገንዘብ ሚኒስቴር የግምጃ ቤት ሰነዱን ለሚገዙት ተቋማት ገንዘቡን ከነወለዱ መክፈል ይጠበቅበታል፡፡
ይህም ወጭውን ስለሚያንረው የበጀት ጉድለቱን እየለጠጠው እንደሚቀጥል የምጣኔ ሐብት ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡
በተጨማሪም መንግስት ገንዘቡን ለመክፈል የሚወስዳቸው ርምጃዎች የህዝብን ኑሮ ጫና ውስጥ ሊከቱ እንደሚችሉ ሰምተናል፡፡
የፖሊሲ ስህተት ትውድን ምን ያህል ዋጋ እንደሚያስከፍል ማሳያ ነውም ተብሏል፡፡
ትዕግስት ዘሪሁን
Comments