ህዳር 4፣2017 በእስራኤል የመከላከያ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ከፍተኛ ሹም የነበሩት ኢያል ዛሚር ሀላፊነታቸው ለቀቁ
- sheger1021fm
- Nov 14, 2024
- 1 min read
በእስራኤል የመከላከያ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ከፍተኛ ሹም የነበሩት ኢያል ዛሚር ሀላፊነታቸው ለቀቁ፡፡
ከሳምንት በፊት የቀድሞው የመከላከያ ሚኒስትር ዮአብ ጋላንት በጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ ከኃላፊነት እንደተባረሩ ሚድል ኢስት ሞኒተር አስታውሷል፡፡
የኢያል ዛሚር ሀላፊነት መልቀቅም ከዮአብ ጋላንትን መባረር የተከተለ ነው ተብሏል፡፡
ይሁንና ዛሚር ሀላፊነታቸውን የለቀቁበት ምክንያት በዝርዝር አልተጠቀሰም ተብሏል፡፡
የእስራኤል የመከላከያ ሚኒስቴር ሚስጥራዊ መረጃዎችን ለመገናኛ ብዙሃን በማሾለክ ውዝግብ ሲታመስ መሰንበቱ ይነገራል፡፡
በሚስጥሩ ማፈትለክ የተነሳ በጦር ካቢኔው ውስጥ የሚደረግ ምክክር እንዳይቀረፅ መከልከሉ ተጠቅሷል፡፡
የኔነህ ከበደ
Commentaires