ስምምነቱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሽፈራሁ ተሊላ እና የአዋሽ ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ፀሀይ ሽፈራሁ ተፈራርመዋል።
በስመምነቱ መሰረት ወርሃዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ክፍያን በሀገሪቱ ያሉ ሁሉም ባንኮች ያላቸውን የከፍያ ሥርዓት አዋሽ ባንክ ካሰናዳው የመክፈያ ስርዓት ጋር በማስተሳሰር ደንበኞች ክፍያ እንዲፈጽሙ የሚያስችል ነው ተብሏል።
የመክፈያ ስርዓቱ መጀመር የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከሁሉም የፋይናንስ ተቋማት ጋር ሲስተሙን ማስተሳሰር ሳይጠበቅበት፣ በቀጥታ ከአዋሽ ባንክ ሲስተም ጋር እንዲያስተሳሰሩ በማድረግ፣ ለሲስተም ማስተሳሰር የሚያወጣዉን ክፍተኛ ወጪ ያስቀርለታል ሲሉ የአዋሽ ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ፀሀይ ሽፈራሁ ተናግረዋል ።
የአዋሽ ባንክ ደንበኞች በባንኩ ቅርንጫፎች፣ በአዋሽ ብር-ፕሮ የሞባይል ባንኪንግ መተግበርያ አማካይነት የኤሌክትሪክ ፍጆታቸውን መክፈል ይችላሉ ሲሉ ስራ አስፈጻሚው አስረድተዋል።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከአዋሽ ባንክ ጋር ያደረኩት ስምምነት የደንበኞቼን የአገልግሎት እርካታ ለመጨመር የሚሰራ ስራ አካል ነው ብሏል።
የአገልግሎቱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሽፈራሁ ተሊላ አገልግሎቱ በንግድ ባንክ እና በቴሌ ብር አማካይነት የኤሌክትሪክ ፍጆታ ክፍያ እንደሚቀበል አስታውሰዋል።
ይሁን እንጂ የመክፈያ ስርዓቱ በዚህ በመወሰኑ ደንበኞች ቅሬታ ሲያቀርቡ እንደነበር ተናግረዋል።
በዚህም መሰረት ስርዓቱን መዘርጋት ማስፈለጉን ጠቅሰዋል።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት 5 ሚሊዮን ደንበኞች አሉኝ ያለ ሲሆን ደንበኞቼ የፍጆታ ክፍያቸውን በአሻቸው የክፍያ አማራጭ እንዲከፍሉ አማራጩን እያስፋፋሁ እሄዳለሁ ብሏል።
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqz
コメント