ሕብረት ኢንሹራንስ ለሶስት ግብረ ሰናይ ድርጅቶች 1.6 ሚሊዮን ብር ሰጠ።
ኩባንያው 1.6 ሚሊዮን ብር ለግብረ ሰናይ ድርጅቶች የሰጠው የተመሰረተበትን 30ኛ ዓመት ክብረ በዓል ምክንያት በማድረግ ነው።
ኩባንያው በዚሁ መሠረት ለመቄዶንያ የአረጋውያንና የአእምሮ ህሙማንን መርጃ ማዕከል 1 ሚሊየን ብር፣ ለህብረት ለበጎ በጎ አድራጎት ማህበር 400,000 ብር እና ለእውን በጎ አድራጎት ማህበር 200,000 ብር ድጋፍ አድርጓል።
ሕብረት ኢንሹራንስ የተመሰረተበትን 30ኛ ዓመት ክብረ በዓል በትናንትናው ዕለት ባለአክሲዮኖችና እንግዶች በተገኙበት አክብሯል።
ለኩባንያው መስራች አባቶች ለእነ ኢየሱስወርቅ ዛፍ፣ ለደንበኞቹና በ30 ዓመት ጉዞው የላቀ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ግለሰቦች እና ተቋማት እውቅናና ሽልማት ተሰጥቷል።
በሥነ - ሥርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የሕብረት ኢንሹራንስ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ መሠረት በዛብህ ኩባንያው "በ30 ዓመታት ታሪኩ ታላቅና አስደናቂ ዕድገት አስመዝግቧል’’ ብለዋል።
25 ሚሊዮን የተፈረመ እና በ8 ሚሊዮን ብር የተከፈለ ካፒታል የዛሬ 30 ዓመት ነው የተመሰረተው ሕብረት ኢንሹራንስ በአሁኑ ሰዓት የተፈረመ ከፒታሉ 1.5 ቢሊዮን ብር፣ ሙሉ በሙሉ የተከፈለ ካፒታሉ ደግሞ 1.1 ቢሊዮን ብር ሲሆን ጠቅላላ ሃብቱም ብር 4.5 ቢሊዮን ብር ደርሷል ተብሏል፡፡
ኩባንያው ባለፈው የበጀት ዓመት ከግብር በፊት 612 ሚሊዮን ብር ትርፍ አግኝቻለሁ ሲልም አስረድቷል፡፡
ንጋቱ ሙሉ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌YouTube: https://t.ly/9uH-g
📌: Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comments