top of page

ህዳር 6፣ 2017 - ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገራት የሚመጣባትን የፀጥታ ስጋት ለመከላል ህጋዊ መሰረት አላት ተባለ

ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገራት የሚመጣባትን የፀጥታ ስጋት ለመከላል በየትኛውም ሁኔታ ቢሆን እራሷን የመጠበቅ ህጋዊ መሰረት አላት ተባለ፡፡


የሶማሊያ መከላከያ ሚኒስትር በቅርቡ የአፍሪካ ህብረት ሰላም አስከባሪ ሆኖ እንደ አዲስ በሚቋቋመው ስብስብ ውስጥ #የኢትዮጵያ_ሰራዊት አይኖርም ማለታቸው የሚታወስ ሲሆን በዚህ ነጥብ ዙሪያ የውጪ ጉዳይ መ/ቤት ማብራሪያ ተጠይቆ ምላሽ ሰጥቷል፡፡


የሚኒስትሩ ቃል አቀባይ አምባሳደር ነቢያት ለጥያቄው በሰጡት ምላሽ የኢትዮጵያ ሰራዊት ለ #ሶማሊያ ሀገር መሆንና መረጋጋት የከፈለውን ዋጋ አለም ያውቀዋል፤ ስጋት እስከማይሆንበት ደረጃ እስኪደርስም ኢትዮጵያ ትግሏን ትቀጥላለች ብለዋል፡፡


የኔነህ ሲሳይ


ሙሉ ዘገባውን በድምፅ ለማድመጥ




የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


📌 Website: https://shorturl.at/yCz7q


📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g


📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s


Comments


bottom of page