የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከምሁራን ምክንያታዊ የሆነ የሰላ ትችት እጠብቃለሁ አለ፡፡
ኮሚሽኑ ይህን የተናገረው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ንግድ ስራ ኮሌጅ ከመላ ሀገሪቱ ዩኒቨርሲቲዎች ከተወጣጡ ምሁራን ጋር እያደረገ ባለው ውይይት ላይ ነው፡፡
በሒደት ላይ ያለው #ሀገራዊ_ምክክር እውን እንዲሆን የምሁራን ድርሻ ከፍተኛ ነው የተባለ ሲሆን ምክክሩ ድንገት ባይሳካ እንኳን ተወቃሽ የምንሆነው እኛ 11 ኮሚሽነሮች ብቻ ሳንሆን ሁላችንም ነን ሲሉ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽነር አምባሳደር መሐሙድ ድሪል ተናግረዋል፡፡
በኢትዮጵያ ሕዝቡ ከፍተኛ ተስፋ የጣለበትን የምክክር ሂደት እውን እንዲሆን #ምሁራን ምክንያታዊ የሆነ የሰላ ትችት እንዲያቀርቡም ኮሚሽነር አምባዬ ኡጋቶ(ዶ/ር) ጠይቀዋል፡፡
ምሁራን ግምት ላይ የተመሰረተ ትችቶችና ትንታኔዎች በመቃወም ምክንያታዊ የሆነ ትችት ለኮሚሽኑ እንዲያቀርቡ ተጠይቀዋል፡፡
ምሁራን፤ ከሚለያዩ፣ ከሚከፋፍሉ ትርክቶች ወጥተው አብሮ የመኖር የመቻቻል #ትርክቶችን ስለሚደመጡ መፍጠር እንደሚችሉ ኮሚሽነር አምባዬ አስረድተዋል፡፡
‘’በምክክር ሂደቱ የመደመጥ እድል ስላላችሁ ሀገርን የማዳንም፣ የመግደልም አቅሙ አላችሁ እናንተ የማዳኑን መንገድ ከምክክር ኮሚሽኑ ጋር በመስራት እንደምትወጡ ተስፋ አደርጋው’’ ሲሉ ኮሚሽነር አምባዬ ኡጋቶ አስረድተዋል፡፡
የኮሚሽኑ አውን ያለበትን ተግዳሮቶችን ችግሮች ያቀረቡት ኮሚሽነር ተገኝወርቅ ጌጡ በሀገሪቱ የቀጠለው ግጭቶች ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሶ ለመስራት እንቅፋት ሆኗል ብለዋል፡፡
ሁሉንም የኮሚሽኑ እንቅስቃሴ በሊህቃንና ከተሞች አካባቢ በጥርጣሬ ዓይን ማየት ሌላው እንቅፋት ነው ተብሏል፡፡
የፖለቲካ ቁርጠኝነት ከሁሉም ወገን አለመኖሩና ዳር ሆኖ ነገሮችን መመልከት ሌላው ኮሚሽኑ የገጠመው #ችግር መሆኑን ኮሚሽነር ተገኝወርቅ ጠቁመዋል፡፡
በአጠቃላይ የገለልተኝነት እና የአካታችን ጥያቄም በኮሚሽኑ ላይ ስለሚነሱ ሌላው እያደረኩ ባለው እንቅስቀሳሴ እንቅፋት ከሆኑብኝ ችግሮች መካከል ነው ብለዋል፡፡
ያሬድ እንዳሻው
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comments