top of page

ህዳር 8፣2016 ‘’ ኢትዮጵያ ከምኞትና ፍላጎት ባሻገር በቅርቡ የራሷን ወደብ የማግኘት እድሏ ጠባብ ነው’’

  • sheger1021fm
  • Nov 18, 2023
  • 1 min read

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ኢትዮጵያ የእራሷ ወደብ ያስፈልጋታል የሚለው ወሬ በተለይ በመንግስታዊ የመገናኛ ብዙሃን እየተተነተነ ነው፡፡


የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲም ከጂኦ ፖለቲካዊ፣ ከኢኮኖሚያዊና ከህግ እንዲሁም ከዲፕሎማሲ ረገድ ፍትሃዊ የወደብ አጠቃቀምን በተመለከተ ልዩ ምክክር አካሂዶበታል፡፡


በምክክሩ ላይ የቀረበው የመነሻ ፅሁፍ እንደሚያሳየው ኢትዮጵያ ከምኞት እና ፍላጎት ባሻገር በቅርቡ የራሷን የባህር በር የማግኘት እድል የላትም፡፡


ለምን? ጉዳዩንም ከጎረቤት ሀገራት ጋር ካላት ወቅታዊ መስተጋብር፣ እንዲሁም ቀጠናዊና አለም አቀፋዊ ሁኔታዎች አንፃር ተተንትኗል፡፡



ንጋቱ ሙሉ

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqz

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page